የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 9

9
ሳውል እንደ ተጠራ
1ሳውል ግን የጌ​ታን ደቀ መዛ​ሙ​ርት ለመ​ግ​ደል ገና እየ​ዛተ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ሄደ። 2ምን​አ​ል​ባት በመ​ን​ገድ የሚ​ያ​ገ​ኘው ሰው ቢኖር ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እያ​ሰረ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ላሉት ምኵ​ራ​ቦች የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ ከሊቀ ካህ​ናቱ ለመነ። 3ሲሄ​ድም ወደ ደማ​ስቆ ከተማ አቅ​ራ​ቢያ በደ​ረሰ ጊዜ መብ​ረቅ ድን​ገት ከሰ​ማይ ብልጭ አለ​በት። 4በም​ድር ላይም ወደቀ፤ ወዲ​ያ​ውም፥ “ሳውል፥ ሳውል፥ ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?” የሚ​ለ​ውን ቃል ሰማ። 5ሳው​ልም፥ “አቤቱ፥ አንተ ማነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ነኝ፤ በሾለ ብረት ላይ ብት​ቆም ለአ​ንተ ይብ​ስ​ሃል”#“በሾ​ለው ብረት ላይ ብት​ቆም ለአ​ንተ ይብ​ስ​ሃል” የሚ​ለው በአ​ን​ዳ​ንድ የግ​ሪክ ዘርዕ አይ​ገ​ኝም። አለው። 6እር​ሱም እየ​ፈ​ራና እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ርግ ትሻ​ለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነ​ሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚ​ያም ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን ይነ​ግ​ሩ​ሃል” አለው። 7ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሰዎች ድምፅ እየ​ሰሙ ማን​ንም ሳያዩ ተደ​ን​ቀው ቆሙ። 8ሳው​ልም ከም​ድር ተነሣ፤ ነገር ግን ዐይ​ኖቹ ተገ​ል​ጠው ሳሉ የሚ​ያ​የው ነገር አል​ነ​በ​ረም፤ እየ​መ​ሩም ወደ ደማ​ስቆ አገ​ቡት። 9በዚ​ያም ሳያይ ሳይ​በ​ላና ሳይ​ጠጣ ሦስት ቀን ቈየ።
10በደ​ማ​ስ​ቆም ስሙን ሐና​ንያ የሚ​ሉት አንድ ደቀ መዝ​ሙር ነበር፤ ጌታም በራ​እይ ተገ​ልጦ፥ “ሐና​ንያ” ብሎ ጠራው፤ እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ እነ​ሆኝ” አለ። 11ጌታም፥ “ተነ​ሣና ቅን በም​ት​ባ​ለው መን​ገድ ሂድ፤ በይ​ሁዳ ቤትም ከጠ​ር​ሴስ ሀገር የመጣ ሳውል የሚ​ባል ሰው ፈልግ፤ እርሱ አሁን ይጸ​ል​ያ​ልና” አለው። 12ሳው​ልም በራ​እይ ሐና​ንያ የሚ​ባል ሰው ወደ እርሱ ገብቶ ያይ ዘንድ እጁን ሲጭ​ን​በት አየ። 13ሐና​ንያ ግን መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለ​ዚህ ሰው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በቅ​ዱ​ሳ​ኖ​ችህ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰም​ቻ​ለሁ። 14ወደ​ዚ​ህም ከካ​ህ​ናቱ አለቃ አስ​ፈ​ቅዶ የመጣ ስም​ህን የሚ​ጠ​ሩ​ትን ሁሉ ሊያ​ስር ነው።” 15ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፊት ስሜን ይሸ​ከም ዘንድ ለእኔ የተ​መ​ረጠ ዕቃ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና። 16እኔም ስለ ስሜ መከ​ራን ይቀ​በል ዘንድ እን​ዳ​ለው አሳ​የ​ዋ​ለሁ።” 17ያን​ጊ​ዜም ሐና​ንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁ​ንም ጫነ​በ​ትና፥ “ወን​ድሜ ሳውል፥ በመ​ን​ገድ ስት​መጣ የታ​የህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ታይና መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​ብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው። 18ያን​ጊ​ዜም ፈጥኖ እንደ ቅር​ፊት ያለ ነገር ከዐ​ይ​ኖቹ ላይ ተገፎ ወደቀ፤ ዐይ​ኖ​ቹም ተገ​ለጡ፤ ወዲ​ያ​ውም አየ፤ ተነ​ሥ​ቶም ተጠ​መቀ። 19እህ​ልም በላ፤ በረ​ታም፤ ጥቂት ቀንም ከደቀ መዛ​ሙ​ርት ጋር በደ​ማ​ስቆ ሰነ​በተ። 20ወዲ​ያ​ው​ኑም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነው” ብሎ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በየ​ም​ኵ​ራ​ቦቹ ሰበከ፥ አስ​ተ​ማ​ረም። 21የሰ​ሙ​ትም ሁሉ አደ​ነቁ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይህን ስም የሚ​ጠ​ሩ​ትን ሁሉ ይጠ​ላ​ቸው የነ​በ​ረው ይህ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ዚህ ወደ​ዚህ የመ​ጣው እያ​ሰረ ወደ ሊቀ ካህ​ናቱ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?” 22ሳውል ግን እየ​በ​ረታ ሔደ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም ለነ​በ​ሩት አይ​ሁድ ይህ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ እያ​ስ​ረዳ መልስ አሳ​ጣ​ቸው።
23 # 2ቆሮ. 11፥32-33። ከብዙ ቀንም በኋላ አይ​ሁድ ሳው​ልን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ተማ​ከሩ። 24ሳውል ግን በእ​ርሱ ላይ ሊያ​ደ​ር​ጉት የሚ​ሹ​ትን ዐወ​ቀ​ባ​ቸው፤ ሊገ​ድ​ሉ​ትም በቀ​ንና በሌ​ሊት የከ​ተ​ማ​ውን በር ይጠ​ብቁ ነበር። 25ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም በሌ​ሊት ወሰ​ዱት፤ በቅ​ር​ጫ​ትም አድ​ር​ገው በቅ​ጽሩ ድም​ድ​ማት ላይ አወ​ረ​ዱት።
26ሳው​ልም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሰ ጊዜ ሊገ​ና​ኛ​ቸው ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን ፈለ​ጋ​ቸው። ሁሉም ፈሩት፤ የጌ​ታ​ችን ደቀ መዝ​ሙር እንደ ሆነ አላ​መ​ኑ​ትም ነበ​ርና። 27በር​ና​ባ​ስም አግ​ኝቶ ወደ ሐዋ​ር​ያት ወሰ​ደው፤ ጌታ​ች​ንም በመ​ን​ገድ እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና እንደ አነ​ጋ​ገ​ረው፥ በደ​ማ​ስ​ቆም በኢ​የ​ሱስ ስም እንደ አስ​ተ​ማረ ነገ​ራ​ቸው። 28በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አብ​ሮ​አ​ቸው ይገ​ባና ይወጣ ነበረ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ስምም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምር ነበር። 29ከግ​ሪክ ሀገር መጥ​ተው የነ​በ​ሩ​ት​ንም አይ​ሁድ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ሊገ​ድ​ሉት ፈለጉ። 30ወን​ድ​ሞ​ችም ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሳ​ርያ አወ​ረ​ዱት፤ ከዚ​ያም ወደ ጠር​ሴስ ላኩት።
31በይ​ሁዳ፥ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ ያሉ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ በሰ​ላም ኖሩ፤ ታነ​ጹም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት ጸን​ተው ኖሩ፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ አጽ​ና​ኝ​ነት በዙ።
ቅዱስ ጴጥ​ሮስ ኤን​ያን እንደ ፈወሰ
32ከዚ​ህም በኋላ ጴጥ​ሮስ በየ​ቦ​ታዉ ሲዘ​ዋ​ወር በልዳ ወደ​ሚ​ኖ​ሩት ቅዱ​ሳን ዘንድ ደረሰ። 33በዚ​ያም ኤንያ የተ​ሰኘ ሰውን አገኘ፤ እር​ሱም ታሞ በአ​ልጋ ከተኛ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ሽባ ነበ​ርና። 34ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ኤንያ ሆይ፥ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይፈ​ው​ስህ፤ ተነ​ሥና አል​ጋ​ህን አን​ጥፍ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ተነሣ። 35በል​ዳና በሳ​ሮና የሚ​ኖ​ሩም ሁሉ እር​ሱን አይ​ተው ወደ ጌታ​ችን ተመ​ለሱ።
ስለ ጣቢታ
36በኢ​ዮጴ ሀገ​ርም ጣቢታ የም​ት​ባል አን​ዲት ደቀ መዝ​ሙር ነበ​ረች፤ በት​ር​ጓ​ሜ​ውም ዶር​ቃስ ይሉ​አ​ታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እር​ስ​ዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽ​ዋ​ትም ትሰጥ ነበር። 37ያን​ጊ​ዜም ታማ ሞተ​ችና በድ​ን​ዋን አጥ​በው በሰ​ገ​ነት አስ​ተ​ኙ​አት። 38ልዳም ለኢ​ዮጴ ቅርብ ነበ​ርና ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጴጥ​ሮስ በዚያ እን​ዳለ ሰም​ተው ወደ እነ​ርሱ መም​ጣት እን​ዳ​ይ​ዘ​ገይ ይማ​ል​ዱት ዘንድ ሁለት ሰዎ​ችን ወደ እርሱ ላኩ። 39ጴጥ​ሮ​ስም ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ በደ​ረ​ሰም ጊዜ ወደ ሰገ​ነት አወ​ጡት፤ ባል​ቴ​ቶ​ችም ሁሉ ወደ እርሱ መጥ​ተው በፊቱ ቆሙ፤ ያለ​ቅ​ሱ​ላ​ትም ነበር፤ ዶር​ቃ​ስም በሕ​ይ​ወት ሳለች የሠ​ራ​ች​ውን ቀሚ​ሱ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አሳ​ዩት። 40ጴጥ​ሮ​ስም ሁሉን ካስ​ወጣ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ ጸለየ፤ ወደ በድ​ን​ዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም ዐይ​ኖ​ች​ዋን ገለ​ጠች፤ ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮ​ስን አየ​ችው፤ ቀና ብላም ተቀ​መ​ጠች። 41እጁ​ንም ለእ​ር​ስዋ ሰጥቶ አስ​ነ​ሣት፤ ቅዱ​ሳ​ን​ንና ባል​ቴ​ቶ​ች​ንም ጠርቶ እር​ስ​ዋን አድኖ ሰጣ​ቸው። 42በኢ​ዮ​ጴም ያሉ ሁሉ ይህን ሰሙ፤ ብዙ​ዎ​ችም በጌ​ታ​ችን አመኑ። 43ጴጥ​ሮ​ስም በኢ​ዮጴ በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት ብዙ ቀን ተቀ​መጠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ