የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 8:27-31

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 8:27-31 አማ2000

ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ሥት የሕ​ን​ደኬ ጃን​ደ​ረባ ከሹ​ሞ​ችዋ የበ​ለጠ፥ በሀ​ብ​ቷም ሁሉ ላይ በጅ​ሮ​ንድ የነ​በረ፥ አንድ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ሊሰ​ግድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ። ሲመ​ለ​ስም በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ያነብ ነበር። መን​ፈስ ቅዱ​ስም ፊል​ጶ​ስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረ​ገላ ተከ​ተ​ለው” አለው። ፊል​ጶ​ስም ፈጥኖ ደርሶ የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ሲያ​ነብ ሰማው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “በውኑ የም​ታ​ነ​በ​ውን ታው​ቀ​ዋ​ለ​ህን?” አለው። ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “ያስ​ተ​ማ​ረኝ ሳይ​ኖር በምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ወጥቶ አብ​ሮት ይቀ​መጥ ዘንድ ፊል​ጶ​ስን ለመ​ነው።