የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 8

8
በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ስለ ደረ​ሰው ስደት
1በዚያ ወራ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትም በቀር ሁሉም በይ​ሁ​ዳና በሰ​ማ​ርያ ባሉ አው​ራ​ጃ​ዎች ሁሉ ተበ​ተኑ። 2እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስ​ንም ደጋግ ሰዎች አን​ሥ​ተው ቀበ​ሩት፤ ታላቅ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት።
ሳውል ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን እንደ አሳ​ደደ
3 # የሐዋ. 22፥4-5፤ 26፥9-11። ሳውል ግን ገና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ይቃ​ወም ነበር፤ የሰ​ው​ንም ቤት ሁሉ ይበ​ረ​ብር ነበር፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እየ​ጐ​ተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስ​ገ​ባ​ቸው ነበር። 4የተ​በ​ተ​ኑት ግን እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰበኩ፥ አስ​ተ​ማ​ሩም። 5ፊል​ጶ​ስም ወደ ሰማ​ርያ ከተማ ወረደ፤ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰበ​ከ​ላ​ቸው። 6ሕዝ​ቡም የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን በሰ​ሙና ያደ​ር​ገው የነ​በ​ረ​ውን ተአ​ም​ራት በአዩ ጊዜ በአ​ንድ ልብ የፊ​ል​ጶ​ስን ነገር ተቀ​በሉ። 7ርኩ​ሳን መና​ፍ​ስት ያደ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ብዙ​ዎች ነበ​ሩና፥ በታ​ላቅ ቃል እየ​ጮኹ ይወጡ ነበር፤ ብዙ​ዎች ልም​ሾ​ዎ​ችና አን​ካ​ሶ​ችም ይፈ​ወሱ ነበር። 8በዚ​ያ​ችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። 9በዚ​ያ​ችም ከተማ ሲሞን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ የሰ​ማ​ርያ ሰዎ​ች​ንም ያስት ነበር፤ ሰው​የዉ ሥራ​የኛ ነበር፤ ራሱ​ንም ታላቅ ያደ​ርግ ነበር። 10ከታ​ና​ና​ሾ​ቹም ጀምሮ እስከ ታላ​ላ​ቆቹ ድረስ “ታላቁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ይህ ነው” እያሉ ሁሉም ያደ​ም​ጡት ነበር። 11ከብዙ ዘመ​ንም ጀምሮ በጥ​ን​ቈ​ላው ያታ​ል​ላ​ቸው ስለ ነበር ያዳ​ም​ጡት ነበር። 12ነገር ግን ፊል​ጶስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትና ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰብ​ኮ​ላ​ቸው በአ​መኑ ጊዜ ሴቶ​ችም ወን​ዶ​ችም ተጠ​መቁ። 13ሲሞ​ንም ወዲ​ያ​ውኑ አምኖ ተጠ​መቀ፤ ፊል​ጶ​ስ​ንም ይከ​ተል ጀመር፤ በፊ​ል​ጶ​ስም እጅ የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ርና ታላቅ ኀይል ባየ ጊዜ ይደ​ነቅ ነበር።
14በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የነ​በሩ ሐዋ​ር​ያ​ትም የሰ​ማ​ርያ ሰዎች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እንደ ተቀ​በሉ በሰሙ ጊዜ ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ዮሐ​ን​ስን ወደ እነ​ርሱ ላኩ​ላ​ቸው። 15ወር​ደ​ውም መን​ፈስ ቅዱ​ስን እን​ዲ​ቀ​በሉ ጸለ​ዩ​ላ​ቸው። 16በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተጠ​መቁ እንጂ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በአ​ንዱ ላይ ስንኳ መን​ፈስ ቅዱስ ገና አል​ወ​ረ​ደም ነበ​ርና። 17በዚያ ጊዜም እጃ​ቸ​ውን ጫኑ​ባ​ቸው፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ተቀ​በሉ። 18ሲሞ​ንም ሐዋ​ር​ያት እጃ​ቸ​ውን በጫ​ኑ​በት ሰው ላይ መን​ፈስ ቅዱስ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ ባየ ጊዜ ገን​ዘብ አመ​ጣ​ላ​ቸ​ውና፥ 19“እጄን በም​ጭ​ን​በት ሰው ላይ መን​ፈስ ቅዱስ ይወ​ርድ ዘንድ ለእ​ኔም ይህን ሥል​ጣን ስጡኝ” አላ​ቸው። 20ጴጥ​ሮስ ግን እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ በገ​ን​ዘብ ልት​ገዛ ዐስ​በ​ሃ​ልና ገን​ዘ​ብህ ከአ​ንተ ጋር ይጥፋ። 21በዚህ ነገር ዕድ​ልና ርስት የለ​ህም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልብህ የቀና አይ​ደ​ለ​ምና። 22አሁ​ንም ከክ​ፋ​ትህ ተመ​ለ​ስና ንስሓ ግባ። የል​ቡ​ና​ህ​ንም ዐሳብ ይተ​ው​ልህ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለምን። 23በመ​ራራ መርዝ ተመ​ር​ዘህ፥ በዐ​መፃ ማሰ​ሪያ ተተ​ብ​ት​በህ የም​ት​ኖር ሆነህ አይ​ሃ​ለ​ሁና።” 24ሲሞ​ንም መልሶ፥ “ካላ​ች​ሁት ሁሉ ምንም እን​ዳ​ይ​ደ​ር​ስ​ብኝ እና​ንተ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ኑ​ልኝ” አለ። 25እነ​ር​ሱም ከመ​ሰ​ከ​ሩና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ከተ​ና​ገሩ በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ በብ​ዙ​ዎች የሰ​ማ​ርያ መን​ደ​ሮ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አስ​ተ​ማሩ።
ስለ ፊል​ጶ​ስና ስለ ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊዉ ጃን​ደ​ረባ
26የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ፊል​ጶ​ስን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በቀ​ትር ጊዜ ተነ​ሣና በደ​ቡብ በኩል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ጋዛ በሚ​ያ​ወ​ር​ደው በም​ድረ በዳው መን​ገድ ሂድ።” 27ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ሥት የሕ​ን​ደኬ ጃን​ደ​ረባ ከሹ​ሞ​ችዋ የበ​ለጠ፥ በሀ​ብ​ቷም ሁሉ ላይ በጅ​ሮ​ንድ የነ​በረ፥ አንድ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ሊሰ​ግድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ። 28ሲመ​ለ​ስም በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ያነብ ነበር። 29መን​ፈስ ቅዱ​ስም ፊል​ጶ​ስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረ​ገላ ተከ​ተ​ለው” አለው። 30ፊል​ጶ​ስም ፈጥኖ ደርሶ የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ሲያ​ነብ ሰማው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “በውኑ የም​ታ​ነ​በ​ውን ታው​ቀ​ዋ​ለ​ህን?” አለው። 31ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “ያስ​ተ​ማ​ረኝ ሳይ​ኖር በምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ወጥቶ አብ​ሮት ይቀ​መጥ ዘንድ ፊል​ጶ​ስን ለመ​ነው። 32ያነ​በው የነ​በረ የመ​ጽ​ሐፉ ቃልም እን​ዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሚ​ሸ​ል​ተው ፊት እን​ደ​ማ​ይ​ና​ገር እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም። 33#ኢሳ. 53፥7-8። በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዶ​አ​ልና ትው​ል​ዱን ማን ይና​ገ​ራል?” 34ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም ለፊ​ል​ጶስ መልሶ፥ “ነቢዩ ስለ ማን እን​ዲህ ይላል? ስለ ራሱ ነውን? ወይስ ስለ ሌላ? እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለው። 35ፊል​ጶ​ስም አፉን ከፈተ፤ ስለ ኢየ​ሱ​ስም ከዚ​ያው መጽ​ሐፍ ጀምሮ አስ​ተ​ማ​ረው። 36በመ​ን​ገድ ሲሄ​ዱም ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “እነሆ፥ ውኃ፥ መጠ​መ​ቅን ምን ይከ​ለ​ክ​ለ​ኛል?” አለው። 37ፊል​ጶ​ስም፥ “በፍ​ጹም ልብህ ብታ​ምን ይገ​ባ​ሃል” አለው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ አም​ና​ለሁ” አለው። 38ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ቆሙ አዘዘ፤ አቁ​መ​ውም ፊል​ጶ​ስና ጃን​ደ​ረ​ባው በአ​ን​ድ​ነት ወደ ውኃው ወረዱ፤ አጠ​መ​ቀ​ውም። 39ከው​ኃ​ዉም ከወጡ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፊል​ጶ​ስን ነጥቆ ወሰ​ደው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ዉም ከዚያ ወዲያ አላ​የ​ውም፤ ደስ እያ​ለ​ውም መን​ገ​ዱን ሄደ። 40ፊል​ጶ​ስም አዛ​ጦን ወደ​ም​ት​ባል ሀገር ደረሰ፤ በከ​ተ​ማ​ዎ​ችም ሁሉ እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወረ ወደ ቂሳ​ርያ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ያስ​ተ​ምር ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ