የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 23

23
1ጳው​ሎ​ስም በአ​ደ​ባ​ባዩ ወደ​አ​ሉት ሰዎች አተ​ኵሮ ተመ​ለ​ከ​ተና፥ “እና​ንተ ሰዎች ወን​ድ​ሞች፥ እኔስ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ በመ​ል​ካም ሕሊና ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሳገ​ለ​ግል ኑሬ​አ​ለሁ” አላ​ቸው። 2ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ግን ጳው​ሎ​ስን አፉን እን​ዲ​መ​ቱት በአ​ጠ​ገቡ ቆመው የነ​በ​ሩ​ትን#“በአ​ጠ​ገቡ ቆመው የነ​በ​ሩ​ትን” የሚ​ለው በግ​እዙ የለም። አዘዘ። 3#ማቴ. 23፥27-28። ጳው​ሎ​ስም መልሶ፥ “አንተ የተ​ለ​ሰነ ግድ​ግዳ በሕግ ልት​ፈ​ር​ድ​ብኝ ተቀ​ም​ጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝ​ዛ​ለ​ህን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ሃል” አለው። 4በአ​ጠ​ገቡ ቆመው የነ​በ​ሩ​ትም ጳው​ሎ​ስን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሾ​መ​ውን ሊቀ ካህ​ናት እን​ዴት ትሳ​ደ​ባ​ለህ?” አሉት። 5#ዘፀ. 22፥28። ጳው​ሎ​ስም፥ “ወን​ድ​ሞች፥ ሊቀ ካህ​ናት መሆ​ኑን አላ​ው​ቅም መጽ​ሐፍ ‘በሕ​ዝ​ብህ አለቃ ላይ ክፉ አት​ና​ገር’ ይላ​ልና” አላ​ቸው።
6 # የሐዋ. 26፥5፤ ፊል. 3፥5። ጳው​ሎ​ስም እኩ​ሌ​ቶቹ ሰዱ​ቃ​ው​ያን እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ፈሪ​ሳ​ው​ያን እንደ ሆኑ ዐውቆ፥ “እኔ ፈሪ​ሳዊ የፈ​ሪ​ሳዊ ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስ​ፋና ስለ ሙታን መነ​ሣ​ትም ይፈ​ረ​ድ​ብ​ኛል” ብሎ በአ​ደ​ባ​ባይ ጮኸ። 7እን​ዲ​ህም ባለ ጊዜ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንና ሰዱ​ቃ​ው​ያን ተጣሉ፤ ሸን​ጎ​ውም ተከ​ፋ​ፈለ። 8#ማቴ. 22፥23፤ ማር. 12፥18፤ ሉቃ. 20፥27። ሰዱ​ቃ​ው​ያን፥ “ሙታን አይ​ነ​ሡም፤ መል​አ​ክም የለም፤ መን​ፈ​ስም የለም” ይላ​ሉና፤ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ግን ይህ ሁሉ እን​ዳለ ያም​ናሉ። 9ታላቅ ውካ​ታም ሆነ፤ ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ወገን የሆኑ ጸሐ​ፍት ተነ​ሥ​ተው ይጣ​ሉና ይከ​ራ​ከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ነው ክፉ ነገር የለም፤ መን​ፈስ#የግ​እዙ ዘር “መን​ፈስ ቅዱስ” ይላል። ወይም መል​አክ ተና​ግ​ሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አን​ጣላ” አሉ። 10እጅ​ግም በታ​ወኩ ጊዜ ጳው​ሎ​ስን እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቁት የሻ​ለ​ቃው ፈራና መጥ​ተው ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አው​ጥ​ተው ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ወታ​ደ​ሮ​ቹን አዘዘ። 11በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሌሊት ጌታ​ችን ለጳ​ው​ሎስ ተገ​ልጦ፥ “ጽና፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምስ​ክር እንደ ሆን​ኸኝ እን​ዲሁ በሮም ምስ​ክር ትሆ​ነ​ኛ​ለህ” አለው።
12በነ​ጋም ጊዜ አይ​ሁድ ተሰ​ብ​ስ​በው፥ ጳው​ሎ​ስን እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉት ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ ተስ​ማ​ም​ተው ተማ​ማሉ። 13ይህ​ንም ለማ​ድ​ረግ የተ​ማ​ማ​ሉት ሰዎች ከአ​ርባ ይበዙ ነበር። 14እነ​ር​ሱም ወደ ሊቃነ ካህ​ና​ትና ወደ መም​ህ​ራን ሄደው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ጳው​ሎ​ስን እስ​ክ​ን​ገ​ድ​ለው ድረስ እነሆ፥ እን​ዳ​ን​በ​ላና እን​ዳ​ን​ጠጣ ፈጽ​መን ተማ​ም​ለ​ናል። 15አሁ​ንም እና​ንተ ከሸ​ን​ጎው ጋር ወደ ሻለ​ቃው ሂዱና የም​ት​መ​ረ​ም​ሩ​ትና የም​ት​ጠ​ይ​ቁት አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጣው ንገ​ሩት፤ እኛ ግን ወደ እና​ንተ ከመ​ድ​ረሱ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ገ​ድ​ለው ቈር​ጠ​ናል።”
16የጳ​ው​ሎ​ስም የእ​ኅቱ ልጅ ምክ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ሄዶ ወደ ወታ​ደ​ሮች ሰፈር ገባና ለጳ​ው​ሎስ ነገ​ረው። 17ጳው​ሎ​ስም ከመቶ አለ​ቆች አን​ዱን ጠርቶ፥ “የሚ​ነ​ግ​ረው ነገር አለና ይህን ልጅ ወደ የሻ​ለ​ቃው አድ​ር​ስ​ልኝ” አለው። 18የመቶ አለ​ቃ​ውም ልጁን ይዞ ወደ የሻ​ለ​ቃው ወሰ​ደ​ውና፥ “የሚ​ነ​ግ​ርህ ስለ አለው እስ​ረ​ኛው ጳው​ሎስ ይህን ልጅ ወደ አንተ እን​ዳ​ደ​ር​ሰው ለመ​ነኝ” አለው። 19የሻ​ለ​ቃ​ውም ልጁን በእጁ ይዞ ለብ​ቻው ገለል አድ​ርጎ፥ “የም​ት​ነ​ግ​ረኝ ነገሩ ምን​ድ​ነው?” አለው። 20ልጁም እን​ዲህ አለው፥ “አይ​ሁድ አጥ​ብ​ቀህ የም​ት​መ​ረ​ም​ረው መስ​ለህ ጳው​ሎ​ስን ነገ ወደ ሸንጎ ታወ​ር​ድ​ላ​ቸው ዘንድ ሊማ​ል​ዱህ እን​ዲህ መክ​ረ​ዋል። 21አንተ ግን እሽ አት​በ​ላ​ቸው፤ ሊገ​ድ​ሉት ሽም​ቀ​ዋ​ልና፤ እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉ​ትም ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ እን​ዲህ የተ​ማ​ማሉ ሰዎች ከአ​ርባ ይበ​ዛሉ፤ አሁ​ንም እስ​ክ​ት​ል​ክ​ላ​ቸው ይጠ​ብ​ቃሉ እንጂ እነ​ርሱ ቈር​ጠ​ዋል።” 22ከዚ​ህም በኋላ፤ የሻ​ለ​ቃው፥ “ይህን ነገር ለእኔ መን​ገ​ር​ህን ለማ​ንም እን​ዳ​ት​ገ​ልጽ” ብሎ አሰ​ና​በ​ተው።
23ከመቶ አለ​ቆ​ችም ሁለ​ቱን ጠርቶ፥ “ከወ​ታ​ደ​ሮች ሁለት መቶ ሰውና ሰባ ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሁለት መቶ ቀስ​ተ​ኞ​ችም ምረጡ፤ ከሌ​ሊ​ቱም በሦ​ስት ሰዓት ወደ ቂሣ​ርያ ይሂዱ” አላ​ቸው። 24አህ​ያም አም​ጥ​ተው ጳው​ሎ​ስን በዚያ አስ​ቀ​ም​ጠው ወደ ቂሣ​ርያ አገረ ገዢ ወደ ፊል​ክስ እን​ዲ​ወ​ስ​ዱት አዘ​ዛ​ቸው። 25እን​ዲህ የም​ትል ደብ​ዳ​ቤም ጻፈ​ለት።
26“ከሉ​ስ​ዮስ ቀላ​ው​ዴ​ዎስ፥ ለክ​ቡር አገረ ገዢ ፊል​ክስ፥ ሰላም ለአ​ንተ ይሁን። 27ይህን ሰው አይ​ሁድ ያዙት፤ ሊገ​ድ​ሉ​ትም ፈለጉ፤ ከወ​ታ​ደ​ሮ​ችም ጋር ተከ​ላ​ከ​ል​ሁ​ለት፥ የሮም ሰው መሆ​ኑ​ንም ዐውቄ አዳ​ን​ሁት። 28በምን ምክ​ን​ያ​ትም እን​ደ​ሚ​ከ​ሱት በደ​ሉን አውቅ ዘንድ ወደ ሸንጎ አቅ​ርቤ መረ​መ​ር​ሁት። 29ስለ ሕጋ​ቸ​ውም ብቻ እንደ ከሰ​ሱት ተረ​ዳሁ፤ ለሞ​ትና ለመ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ ሌላ በደል ግን የለ​በ​ትም። 30አይ​ሁ​ድም በዚህ ሰው ላይ በመ​ሸ​መቅ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን በዐ​ወ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ላክ​ሁት፤ ከሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ አንተ እን​ዲ​መ​ጡና በፊ​ትህ እን​ዲ​ፋ​ረ​ዱት አዝ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደኅና ሁን።”
31ጭፍ​ሮ​ችም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በሌ​ሊት ወሰ​ዱት፤ ወደ አን​ቲ​ጳ​ጥ​ሪ​ስም አደ​ረ​ሱት። 32በማ​ግ​ሥ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር ይሄዱ ዘንድ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ትተው እነ​ርሱ ወደ ሰፈር ተመ​ለሱ። 33ከዚ​ህም በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ገቡ፤ ወደ አገረ ገዢ​ውም ደረሱ፤ የተ​ላ​ከ​ው​ንም ደብ​ዳቤ ለአ​ገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም ወደ እርሱ አቀ​ረ​ቡት። 34ደብ​ዳ​ቤ​ው​ንም ካነ​በበ በኋላ ከማን ግዛት እንደ ሆነ ጠየ​ቀው። ከኪ​ል​ቅያ የመጣ መሆ​ኑ​ንም ባወቀ ጊዜ፦ 35“እን​ኪ​ያስ ከሳ​ሾ​ችህ ሲመጡ እን​ሰ​ማ​ሃ​ለን” አለው፤ በሄ​ሮ​ድ​ስም ግቢ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቁት አዘዘ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ