የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 22:4-8

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 22:4-8 አማ2000

ይህን ትም​ህ​ርት የሚ​ከ​ተሉ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እያ​ሰ​ርሁ ወደ ወህኒ ቤት አሳ​ልፌ በመ​ስ​ጠት እስከ ሞት ድረስ አሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው። እን​ዲ​ቀ​ጡም ከዚያ ያሉ​ትን አስሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ወደ አሉ ወን​ድ​ሞች እን​ድ​ሄድ ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ የተ​ቀ​በ​ል​ኋ​ቸው ሊቀ ካህ​ና​ቱና መም​ህ​ራን ሁሉ ይመ​ሰ​ክ​ራሉ። “ከዚህ በኋላ ወደ ደማ​ስቆ ስሄድ ቀትር በሆነ ጊዜ ወደ ከተ​ማው አቅ​ራ​ቢያ ደርሼ ሳለሁ ድን​ገት ታላቅ መብ​ረቅ ከሰ​ማይ በእኔ ላይ አን​ፀ​ባ​ረቀ። በም​ድር ላይም ወደ​ቅሁ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?’ የሚል ቃል​ንም ሰማሁ። እኔም መልሼ፦ ‘አቤቱ፥ አንተ ማነህ?’ አል​ሁት፤ እር​ሱም፦ ‘አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ነኝ’ አለኝ።