የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ተረፈ ባሮክ 5

5
1ባሮ​ክም ይህን ከተ​ና​ገረ በኋላ ንስሩ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ይዞ በረረ፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ሄዶ በም​ድረ በዳ ባለው ቦታ ከከ​ተማ ውጭ ባለ ዛፍ ላይ ዐረፈ። 2ኤር​ም​ያስ እስ​ኪ​ያ​ልፍ ድረስ ሌሎ​ችም ወገ​ኖች እስ​ኪ​ያ​ልፉ ድረስ በዚ​ያው ቈየ፤ ኤር​ም​ያ​ስም ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን ከወ​ገ​ኖች የሞ​ተ​ውን የም​ቀ​ብ​ር​በት ቦታ ስጠኝ ብሎ ለም​ኗ​ልና፥ እር​ሱም ሰጥ​ቶ​ታ​ልና ሕዝቡ የሞ​ተ​ውን ሰው ሊቀ​ብሩ በዚያ በኩል ዐለፉ። 3ለሞ​ተ​ውም ሰው እያ​ለ​ቀሱ ሲሄዱ ከን​ስሩ ፊት ደረሱ። 4ንስ​ሩም በዚያ ቦታ ሆኖ በታ​ላቅ ቃል አሰ​ምቶ ጮኸ፤ “አም​ላክ የመ​ረ​ጠህ ኤር​ም​ያስ ሆይ፥ ለአ​ንተ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ ሄደህ ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስ​ባ​ቸው፤ እኔ#አን​ዳ​ንድ ዘርዕ “ከባ​ሮ​ክና ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ ያመ​ጣ​ሁ​ትን መል​ካም የም​ሥ​ራች ...” ይላል። ያመ​ጣ​ሁ​ትን መል​ካም የም​ሥ​ራች እስ​ኪ​ሰሙ ድረስ ወደ​ዚህ ይምጡ” አለው።
5ኤር​ም​ያ​ስም ይህን ሰምቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ያን​ጊ​ዜም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰበ​ሰበ፤ እነ​ር​ሱም ንስሩ ወዳ​ለ​በት ደረሱ። 6ንስ​ሩም ሬሳው ወዳ​ለ​በት ወርዶ ረገ​ጠው፤ ሙቱም ተነሣ፤ ይህ​ንም ያደ​ረገ ስለ ተደ​ረ​ገ​ላ​ቸው ተአ​ም​ራት ሕዝቡ ሁሉ ያም​ኑና ያደ​ንቁ ዘንድ ነው። 7እነ​ር​ሱም፥ “ከሙሴ ጋር በም​ድረ በዳ ሳሉ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የታ​ያ​ቸው አም​ላ​ካ​ችን እነሆ፥ ይህ ነው፤ ዛሬም በታ​ላቅ ንስር አም​ሳል ለእኛ የታ​የን እርሱ ነው” አሉ። 8ንስ​ሩም ኤር​ም​ያ​ስን እን​ዲህ አለው፥ “መጥ​ተህ ይህን ደብ​ዳቤ ከፍ​ተህ ለሕ​ዝቡ አን​ብ​ብ​ላ​ቸው።” እር​ሱም ለሕ​ዝቡ አነ​በ​በ​ላ​ቸው።
9ሕዝ​ቡም በሰሙ ጊዜ ሁሉም አንድ ሆነው አለ​ቀሱ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ አመድ ነሰ​ነሱ፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም፥ “ወደ ሀገ​ራ​ችን እን​ገባ ዘንድ ምን እና​ድ​ርግ? ንገ​ረን” አሉት። 10ኤር​ም​ያ​ስም ተነ​ሥቶ፥ “በደ​ብ​ዳቤ የሰ​ማ​ች​ሁ​ትን ሁሉ እን​ደ​ዚሁ አድ​ርጉ ወደ ሀገ​ራ​ች​ሁም ይመ​ል​ሳ​ች​ኋል” አላ​ቸው።
11ኤር​ም​ያ​ስም ለባ​ሮክ እን​ዲህ ብሎ ደብ​ዳቤ ጻፈ፥ “ልጄ ወዳጄ፥ በኀ​ጢ​አ​ተኛ ንጉሥ ትእ​ዛዝ እስ​ክ​ን​ወጣ ድረስ ይቅር ይለን ዘንድ፥ ወደ ጎዳ​ና​ች​ንም ይመ​ራን ዘንድ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እየ​ተ​ገ​ዛህ ስለ እኛ መጸ​ለ​ይን ቸል አት​በል። 12አንተ ግን ወደ ባቢ​ሎን ተማ​ር​ከው ከመጡ ወገ​ኖች ጋር ልት​መጣ ባል​ተ​ወህ በአ​ም​ላክ ፊት ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አገ​ኘህ። 13አንድ ልጅ እን​ዳ​ለው አባት፥ ልጁም ይፈ​ረ​ድ​በት ዘንድ እንደ ተሰጠ፥ የሚ​ያ​ረ​ጋ​ጉት በአ​ባቱ ዘንድ ያሉት ሰዎ​ችም አባቱ በኀ​ዘን ሲጐ​ሰ​ቍል እን​ዳ​ያ​ዩት ፊታ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ሸ​ፍኑ፥ 14እን​ደ​ዚሁ አም​ላ​ክህ አን​ተን ይቅር አለህ፤ እኛም ወደ​ዚህ ሀገር ከደ​ረ​ስን ጀምሮ እስከ ዛሬ ከኀ​ዘን አላ​ረ​ፍ​ን​ምና የሕ​ዝ​ቡን መከራ እን​ዳ​ታይ ወደ ባቢ​ሎን ትመጣ ዘንድ አል​ተ​ወ​ህም። ወደ​ዚህ ሀገር ከመ​ጣን ጀምሮ ለስ​ድሳ ስድ​ስት ዓመ​ታት ከኀ​ዘን አላ​ረ​ፍ​ንም። 15ወደ ንጉሡ ወደ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም አን​ጋ​ጠው እያ​ለ​ቀሱ “አቤቱ፥ የሶ​ሮት አም​ላክ ሆይ፥ ይቅር በለን” የሚሉ ከሕ​ዝቡ አገ​ኘን።
16እኒህ ያዘኑ ሰዎች ሌላ​ውን አም​ላክ ሲጠሩ “ይቅር በለ​ንም” ሲሉ ይህን ነገር በሰ​ማሁ ጊዜ አዝኜ አለ​ቀ​ስሁ። 17ዳግ​መ​ኛም እኔ ሳን​ማ​ረክ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያደ​ረ​ግ​ነ​ውን በዓል ዐሰ​ብሁ፤ ይህ​ንም ዐስቤ እየ​ተ​ጨ​ነ​ቅ​ሁና እያ​ለ​ቀ​ስሁ ወደ ቤቴ እመ​ለስ ነበር። 18አሁ​ንም ከፋ​ርስ ሀገር እን​ዲ​ወጡ ቃሌን ይሰሙ ዘንድ፥ ከአፌ የወ​ጣ​ው​ንም ነገር ይቀ​በሉ ዘንድ ስለ ወገ​ኖ​ቻ​ችን አቤ​ሜ​ሌ​ክና አንተ ባላ​ች​ሁ​በት ቦታ ፈጣ​ሪ​ያ​ች​ንን ለምኑ። 19አሁ​ንም በኖ​ር​ን​በት ዘመን ሁሉ “ፈጣ​ሪ​ያ​ችሁ በጽ​ዮን ከሚ​መ​ሰ​ገ​ን​በት ምስ​ጋና ወገን አዲስ ምስ​ጋ​ናን ንገ​ሩን” ብለው ያዙን ብዬ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ። 20እኛም፥ “በባ​ዕድ ሀገር ሳለን እንደ ምን እን​ዘ​ም​ር​ላ​ች​ኋ​ለን?” አል​ና​ቸው።
21ኤር​ም​ያ​ስም እን​ደ​ዚሁ አድ​ርጎ ጽፎ ደብ​ዳ​ቤ​ውን በን​ስሩ አን​ገት አስሮ “በሰ​ላም ሂድ፤ ጌታም አን​ተን ይጐ​ብ​ኝህ” አለው። 22ንስ​ሩም ደብ​ዳ​ቤ​ውን ይዞ በርሮ ሄደ፤ ደብ​ዳ​ቤ​ው​ንም ወደ ባሮክ አደ​ረሰ፤ ባሮ​ክም ደብ​ዳ​ቤ​ውን ከፍቶ አነ​በ​በው፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ኀዘ​ንና መከራ በሰማ ጊዜ አለ​ቀሰ።
23ኤር​ም​ያስ ግን ያን በለስ ተቀ​ብሎ በሕ​ዝቡ ዘንድ ላሉ በሽ​ተ​ኞች ሰጣ​ቸው። 24የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት እን​ዳ​ይ​ሠሩ እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ተቀ​መጠ። 25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን ከባ​ቢ​ሎን የሚ​ያ​ወ​ጣ​ባት ቀን በደ​ረ​ሰች ጊዜ፥ 26ጌታ ኤር​ም​ያ​ስን እን​ዲህ አለው፥ “አንተ ተነሥ፤ ወገ​ኖ​ች​ህም ይነሡ፤ ወደ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ኑ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የባ​ቢ​ሎ​ንን ሕዝብ ሥራ ይተዉ ዘንድ ጌታ ይወ​ዳል በላ​ቸው። 27ከእ​ና​ንተ ሴቶ​ችን ያገባ ወን​ድን፥ ወን​ዶ​ችን ያገቡ ሴቶ​ች​ንም ፈት​ና​ቸው፤ ቃል​ህን የሰሙ ሰዎ​ችን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መል​ሳ​ቸው፤ ያል​ሰ​ሙ​ህን ሰዎች ግን ወደ እርሷ ይገቡ ዘንድ አት​ተ​ዋ​ቸው።”
28ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲሁ ይህን ሁሉ አነ​በ​በ​ላ​ቸው፤ ሊፈ​ት​ና​ቸ​ውም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ አመ​ጣ​ቸው፤ ጌታም ያላ​ቸ​ውን ይህን ነገር ሲነ​ግ​ራ​ቸው ያገቡ ሰዎች ተለ​ያዩ፤ ሊፋ​ቱም አል​ወ​ደ​ዱም፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም አል​ሰ​ሙ​ትም።
29“ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አን​ተ​ውም፤ ከእኛ ጋራ ወደ ሀገ​ራ​ችን እን​ወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋ​ለን” ያሉ ሰዎ​ችም ነበሩ፤ ከዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ተሻ​ግ​ረው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ። 30ኤር​ም​ያ​ስና ባሮክ፥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም “ከባ​ቢ​ሎን ሴት ያገባ ሰው ሁሉ ወደ ሀገ​ራ​ችን አይ​ገ​ባም” ብለው ተነሡ። 31ሚስት ያገቡ ሰዎ​ችም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን፥ “ተነሡ፤ ወደ ባቢ​ሎን እን​መ​ለስ” አሏ​ቸው ወደ ባቢ​ሎ​ንም ተመ​ል​ሰው ሄዱ። 32የባ​ቢ​ሎ​ንም ሰዎች ባዩ​አ​ቸው ጊዜ ሊቀ​በ​ሏ​ቸው ወጡ፤ “እና​ንተ አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ እኛን ጠል​ታ​ች​ሁ​ና​ልና ከእኛ ተሰ​ው​ራ​ችሁ ወጣ​ችሁ” ብለው ወደ ባቢ​ሎን ይገቡ ዘንድ አል​ተ​ዉ​አ​ቸ​ውም። 33“ከእኛ ተሰ​ው​ራ​ችሁ ስለ ወጣ​ችሁ እና​ን​ተ​ንና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን እን​ዳ​ን​ቀ​በ​ላ​ችሁ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ስም ምለ​ና​ልና ስለ​ዚህ ነገር በደ​ላ​ችሁ፤ ወደ ሀገ​ራ​ች​ንም አት​ገ​ቡም” አሏ​ቸው።
34እን​ደ​ዚ​ያም ያለ​ውን ቃል ሰም​ተው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አው​ራጃ ከተማ አቀኑ፤ ያንም ከተማ ሰማ​ርያ አሉት። 35ኤር​ም​ያ​ስም “ንስሓ ግቡ፤ እነሆ፥ የጽ​ድቅ መል​አክ ይመ​ጣል፤ ለብዙ ዘመ​ንም ወደ​ም​ት​ኖ​ሩ​በት ቦታ​ችሁ ይመ​ል​ሳ​ች​ኋል” ብሎ ወደ እነ​ርሱ ላከ። እነ​ር​ሱም ደስ ብሏ​ቸው ስለ ሕዝቡ መሥ​ዋ​ዕት እየ​ሠዉ ሰባት ቀን ተቀ​መጡ።
36ይህም ከተ​ደ​ረገ በኋላ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ኤር​ም​ያስ ብቻ​ውን ወጣ። 37ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፥ “ለሰው በጎ መዓዛ የም​ት​ሆን አንተ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ ወደ አንተ እስ​ክ​ደ​ርስ ድረስ ዕው​ቀ​ትን የም​ት​ገ​ል​ጥ​ልኝ እው​ነ​ተኛ ዐዋቂ አንተ ነህ። 38ስለ ወገ​ኖ​ችህ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ስለ ተወ​ደ​ደው ስለ ሱራ​ፌል ምስ​ጋና፥ በጎ መዓዛ ስላ​ለው ስለ ኪሩ​ቤ​ልም ዕጣን እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ የጽ​ድቅ ሊቀ መላ​እ​ክት ሚካ​ኤ​ልም በእ​ው​ነት አመ​ስ​ጋኝ ነው፤ የሚ​ያ​በ​ራ​ልኝ፥ ጻድ​ቃ​ንም እስከ ገቡ​ባ​ቸው ድረስ የጽ​ድቅ በሮ​ችን የሚ​ከ​ፍ​ት​ልኝ እርሱ ነው። 39የሁሉ ጌታ አቤቱ፥ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ሁሉን የም​ት​ገዛ ጌታ አንተ ነህ፤ የሚ​ታ​የ​ው​ንና የማ​ይ​ታ​የ​ውን ሁሉ ፈጥ​ረህ የጨ​ረ​ስህ፥ የተ​ሰ​ወ​ረው ሁሉ፥ ሳይ​ፈ​ጠ​ርም ተሰ​ውሮ የነ​በ​ረው ሁሉ በአ​ንተ ዘንድ አለ።”
40ይኽ​ንም ጸለየ፤ ጸሎ​ቱ​ንም ከፈ​ጸመ በኋላ ኤር​ም​ያስ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገብቶ#“ወደ መሠ​ዊ​ያው ገብቶ ...” የሚል ዘርዕ አለ። ቆመ፤ ባሮ​ክና አቤ​ሜ​ሌ​ክም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ ኤር​ም​ያ​ስም ነፍሱ ከሥ​ጋው እንደ ተለ​የች እንደ አንድ ሰው ሆነ። 41ያን​ጊ​ዜም ባሮ​ክና አቤ​ሜ​ሌክ ወድ​ቀው በታ​ላቅ ድምፅ ጮሁ፤ “ወዮ​ልን! የአ​ም​ላክ ካህን አባ​ታ​ችን ኤር​ም​ያስ ከእኛ ተለየ” አሉ። 42ሕዝ​ቡም እን​ዲህ ሰም​ተው ወደ እርሱ ሮጡ፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ወድቆ እንደ ሞተም ሆኖ አገ​ኙ​ትና አለ​ቀሱ፤ ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቀደዱ፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነሰ​ነሱ፤ መራራ ልቅ​ሶ​ንም አለ​ቀሱ።
43የሚ​ቀ​ብ​ሩ​በ​ት​ንም ካዘ​ጋጁ በኋላ “ደኅና ነውና ነፍ​ሱም ዳግ​መኛ ወደ ሥጋው ትመ​ለ​ሳ​ለ​ችና አት​ገ​ን​ዙት” የሚል ቃል መጣ። 44ይህ​ንም ቃል በሰሙ ጊዜ ዳግ​መኛ ነፍሱ ወደ ሥጋው እስ​ክ​ት​መ​ለስ ድረስ እየ​ጠ​በ​ቁት ሦስት ቀን በዙ​ሪ​ያው ተቀ​መጡ እንጂ አል​ገ​ነ​ዙ​ትም። 45በሁ​ሉም መካ​ከል እን​ዲህ የሚል ቃል ተሰማ፤ “በአ​ንድ ቃል አመ​ስ​ግ​ኑት፤ አም​ላ​ካ​ች​ንን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ሁላ​ች​ሁም የአ​ም​ላ​ክን ልጅ መሢ​ሑን አመ​ስ​ግ​ኑት። 46የዓ​ለሙ ሁሉ ብር​ሃን የአ​ም​ላክ ልጅ ኢየ​ሱ​ስም ይፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋል። 47የማ​ይ​ጠፋ ብር​ሃን፥ የሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ሕይ​ወት ነው። 48ከዚህ ዘመን በኋ​ላም ወደ ምድር ለመ​ም​ጣቱ ሦስት መቶ ሠላሳ ሦስት የቀን ሱባዔ ይሆ​ናል።
49“በገ​ነት መካ​ከል ያለ ያል​ተ​ተ​ከለ የሕ​ይ​ወት ዛፍ፥ ዛፎ​ችን ሁሉ ፍሬ እን​ዲ​ያ​ፈሩ፥ የደ​ረ​ቁ​ትም ወደ እርሱ እን​ዲ​መጡ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል። 50ፍሬ እን​ዲ​ያ​ፈሩ፥ እን​ዲ​ለ​መ​ል​ሙና እን​ዲ​ያ​ድ​ጉም ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ ሥሩ ምድ​ርን እን​ዳ​ል​ያዘ ተክል ሥራ​ቸው እን​ዳ​ይ​ደ​ርቅ ለሰ​ማ​ያዊ አም​ላክ ግብ​ርን እን​ስጥ፤ ቀይ መልክ ያለው ቀለ​ምም እንደ ባዘቶ ይነ​ጣል። 51የጣ​ፈ​ጠው ውኃ መራራ ይሆ​ናል፤ መራ​ራ​ውም የጣ​ፈጠ ይሆ​ናል፤ በል​ጁም አን​ደ​በት ፍሬን ያፈሩ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በታ​ላቅ ሐሤ​ትና ደስታ ደሴ​ቶ​ችን ይመ​ር​ቃ​ቸ​ዋል። 52እር​ሱም ራሱ ሰው ሆኖ ወደ​ዚህ ዓለም ይመ​ጣል፤ እኔ ሰው ሆኖ ያየ​ሁት፥ ከአ​ባ​ቱም ወደ​ዚህ ዓለም የሚ​ላ​ከው፥ ሰው ሆኖም ወደ​ዚህ ዓለም የሚ​መ​ጣው፥ እርሱ አብ​ሯ​ቸው ይታይ ዘንድ፥ ይገ​ለ​ጥ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ ዐሥራ ሁለት ሐዋ​ር​ያ​ትን ለእ​ርሱ ይመ​ር​ጣል፤ ወደ ደብረ ዘይ​ትም ይሄ​ዳል፤ የተ​ራ​በ​ች​ንም ነፍስ ሁሉ ያጠ​ግ​ባል።” 53ወደ​ዚህ ዓለም እን​ደ​ሚ​መጣ ኤር​ም​ያስ የአ​ም​ላ​ክን ልጅ ነገር እን​ዲህ ተና​ገረ።
54ሕዝ​ቡም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ ኤር​ም​ያስ፥ “የአ​ም​ላ​ክን ልጅ አም​ላ​ክን አየ​ሁት” ብሎ ስለ ተና​ገ​ረው ስለ​ዚህ ነገር ተቈጡ፤ እነ​ሆም፥ “በኢ​ሳ​ይ​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ግን በእ​ር​ሱም እና​ድ​ር​ግ​በት፤ ተነሡ” አሉ። እኩ​ሌ​ቶቹ፥ “በደ​ን​ጊያ ወግ​ረን እን​ግ​ደ​ለው እንጂ አይ​ሆ​ንም” አሉ። 55ባሮ​ክና አቤ​ሜ​ሌ​ክም፥ “በዚች ሞት አት​ግ​ደ​ሉት” ብለው ጮሁ​ላ​ቸው፤ ባሮ​ክና አቤ​ሜ​ሌ​ክም ስለ ኤር​ም​ያስ አዘኑ። 56ዳግ​መ​ኛም ያያ​ቸ​ውን የተ​ሰ​ወሩ ምሥ​ጢ​ሮ​ችን ይነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ አል​ተ​ዉ​ትም፤ ኤር​ም​ያ​ስም፥ “ያየ​ሁ​ትን ሁሉ እስ​ካ​ስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ድረስ እኔን መግ​ደል አይ​ች​ሉ​ምና አታ​ል​ቅሱ” አላ​ቸው። 57“አሁ​ንም አን​ዲት ድን​ጋይ አም​ጡ​ልኝ፤” አላ​ቸው፥ እነ​ር​ሱም አን​ዲት ድን​ጋይ አመ​ጡ​ለት፤ እር​ሱም አቆ​ማት፤ “የዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃን ሆይ፥ ይህ​ቺን ድን​ጋይ እንደ እኔ ትሆን ዘንድ አድ​ር​ግ​ልኝ” አለ። 58ያን​ጊ​ዜም ድን​ጋዩ ኤር​ም​ያ​ስን በመ​ልክ የሚ​መ​ስ​ለው ሆነ፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም መሰ​ላ​ቸ​ውና ድን​ጋ​ዩን በድ​ን​ጋይ ይደ​በ​ድቡ ጀመር፤ ወን​ጀ​ል​ንም ጨረሱ። 59ኤር​ም​ያስ ግን ያያ​ቸ​ውን ምሥ​ጢ​ሮች ሁሉ ለባ​ሮ​ክና ለአ​ቤ​ሜ​ሌክ ነገ​ራ​ቸው፤ ይህ​ንም ነግ​ሯ​ቸው ከጨ​ረሰ በኋላ ምግ​ብ​ና​ውን ይፈ​ጽም ዘንድ ወደደ፤ ሄዶም በሕ​ዝቡ መካ​ከል ቆመ።
60ያን​ጊ​ዜም ያ ድን​ጋይ፥ “እና​ንት ሰነ​ፎች የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ ኤር​ም​ያ​ስን መስ​ያ​ችሁ በድ​ን​ጋይ ስለ ምን ትደ​በ​ድ​ቡ​ኛ​ላ​ችሁ? ኤር​ም​ያ​ስስ እነሆ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ቁሟል” ብሎ ጮኸ። 61ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ባዩት ጊዜ ብዙ ድን​ጋይ ይዘው ወደ እርሱ ሮጡ፤ እር​ሱም ምስ​ክ​ር​ነ​ቱን ጨረሰ፤ ባሮ​ክና አቤ​ሜ​ሌ​ክም መጥ​ተው ቀበ​ሩት፤ ያንም ድን​ጋይ አም​ጥ​ተው በመ​ቃ​ብሩ አፍ እንደ መዝ​ጊያ አድ​ር​ገው አኖ​ሩት። 62“የኤ​ር​ም​ያስ ረዳቱ እነሆ፥ ይህ ድን​ጋይ ነው” ብለው በው​ስጡ ጻፉ፤ የኤ​ር​ም​ያ​ስም የቀ​ረች ነገሩ እነሆ፥ በባ​ሮክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፋ​ለች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ