መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ 7
7
1ዳዊት፥ “በእግዚአብሔር አመንሁ፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል” ብሎ እንደ ተናገረ በእግዚአብሔር በሚያምኑ ሰዎች ግን ፍርሀትና ድንጋጤ የለባቸውም። 2ዳግመኛም አለ፥ “አርበኞች ቢከቡኝ፥ እኔ በእርሱ አመንሁ፤ እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት፤ እርስዋንም እፈልጋለሁ፥ በእርሱም ያመነ ለዘለዓለሙ በሕይወት ይኖራል፥ ከክፉ ነገርም የተነሣ አይፈራም።” 3በእግዚአብሔር አምኖ ያፈረ ሰው ማን ነው? ጠርቶትስ ቸል ያለው ማን ነው? 4“የወደደኝን እወደዋለሁ፤ ያከበረኝንም አከብረዋለሁ፤ ወደ እኔ የተመለሰውንም እጠብቀዋለሁ” ብሏልና እርሱን ተስፋ አድርጎ ያፈረ ሰው ማን ነው? 5የባልቴቲቱን ሰውነት አድኑ፤ በክፉ ነገር ከሚቃወማችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ያድናችሁ ዘንድ አድኗቸው፤ ጠብቋቸውም፤ ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁን ያድናቸዋል፤ የጻድቃን ልጆች ይባረካሉና፤ አትርፈውም ይሰጣሉ እንጂ እህልን አይቸገሩም።
Currently Selected:
መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ 7: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ