መጽ​ሐፈ መቃ​ብ​ያን ሣልስ 7

7
1ዳዊት፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመ​ንሁ፤ አል​ፈ​ራም፤ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል” ብሎ እንደ ተና​ገረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ያ​ምኑ ሰዎች ግን ፍር​ሀ​ትና ድን​ጋጤ የለ​ባ​ቸ​ውም። 2ዳግ​መ​ኛም አለ፥ “አር​በ​ኞች ቢከ​ቡኝ፥ እኔ በእ​ርሱ አመ​ንሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ዲት ነገር ለመ​ን​ሁት፤ እር​ስ​ዋ​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ፥ በእ​ር​ሱም ያመነ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፥ ከክፉ ነገ​ርም የተ​ነሣ አይ​ፈ​ራም።” 3በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምኖ ያፈረ ሰው ማን ነው? ጠር​ቶ​ትስ ቸል ያለው ማን ነው? 4“የወ​ደ​ደ​ኝን እወ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ያከ​በ​ረ​ኝ​ንም አከ​ብ​ረ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔ የተ​መ​ለ​ሰ​ው​ንም እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለሁ” ብሏ​ልና እር​ሱን ተስፋ አድ​ርጎ ያፈረ ሰው ማን ነው? 5የባ​ል​ቴ​ቲ​ቱን ሰው​ነት አድኑ፤ በክፉ ነገር ከሚ​ቃ​ወ​ማ​ችሁ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ና​ችሁ ዘንድ አድ​ኗ​ቸው፤ ጠብ​ቋ​ቸ​ውም፤ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ልጆ​ቻ​ች​ሁን ያድ​ና​ቸ​ዋል፤ የጻ​ድ​ቃን ልጆች ይባ​ረ​ካ​ሉና፤ አት​ር​ፈ​ውም ይሰ​ጣሉ እንጂ እህ​ልን አይ​ቸ​ገ​ሩም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ