የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 8

8
ዳዊት በጦ​ር​ነት ያገ​ኘው ድል
(1ዜ.መ. 18፥1-17)
1ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ዳዊ​ትም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ምር​ኮን#ዕብ. “ሜቴግ አማ” ይላል። ወሰደ።
2ዳዊ​ትም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን መታ፤ በም​ድ​ርም ጥሎ በገ​መድ ሰፈ​ራ​ቸው፤ በሁ​ለ​ትም ገመድ ለሞት፥ በአ​ን​ድም ገመድ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሁ​ለት ...” ይላል። ለሕ​ይ​ወት ሰፈ​ራ​ቸው፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።
3ዳዊ​ትም ደግሞ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ግዛት ለማ​ስ​ፋ​ፋት በሄደ ጊዜ የሱ​ባን ንጉሥ የረ​አ​ብን ልጅ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ። 4ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ሺህ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን፥ ሰባት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞ​ችን ያዘ፤ ዳዊ​ትም የሰ​ረ​ገ​ለ​ኛ​ውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራ​ሱም መቶ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን ብቻ አስ​ቀረ። 5ከደ​ማ​ስ​ቆም ሶር​ያ​ው​ያን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን ሊረዱ መጡ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ። 6ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮች አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ጠበ​ቀው። 7ዳዊ​ትም ለሱ​ባን ንጉሥ ለአ​ድ​ር​አ​ዛር አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን ጋሻ አግ​ሬ​ዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አመ​ጣ​ቸው።#የሚ​ቀ​ጥ​ለው ዐ. ነገር በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ ነው። እነ​ዚ​ህ​ንም የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ዘመን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ወሰ​ዳ​ቸው። 8ንጉ​ሡም ዳዊት ከሶ​ቤ​ቅና ከተ​መ​ረ​ጡት ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ከተ​ሞች እጅግ ብዙ ናስን ወሰደ። በእ​ር​ሱም ሰሎ​ሞን የብ​ረት ባሕ​ርና ምሰ​ሶ​ዎ​ችን፥ ሰኖ​ች​ንና ሌሎች ዕቃ​ዎ​ችን ሠራ።
9የሓ​ማ​ትም ንጉሥ ታይ ዳዊት የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ። 10ታይም የአ​ድ​ር​አ​ዛር ጠላት ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ስለ ተዋ​ጋ​ውና ስለ ገደ​ለው፥ ታይ ልጁን ኢያ​ዱ​ራን ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይቅ ዘንድ፥ ይመ​ር​ቀ​ውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እር​ሱም የብ​ርና የወ​ርቅ የና​ስም ዕቃ ይዞ መጣ፤ 11እር​ሱ​ንም ንጉሥ ዳዊት ከሀ​ገ​ሮች ሁሉ አም​ጥቶ ከቀ​ደ​ሰው ከወ​ር​ቁና ከብሩ ጋር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ፤ 12ይኸ​ውም ከሶ​ርያ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኤይም” ይላል። ከሞ​ዓ​ብና ከአ​ሞን ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም፥ ከረ​አ​ብም ልጅ ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ምርኮ ያመ​ጣው ነው።
13ዳዊ​ትም በተ​መ​ለሰ ጊዜ ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎች በጨው ሸለቆ ውስጥ በመ​ም​ታቱ ስሙ ተጠራ። 14መላ​ዋን ኤዶ​ም​ያ​ስን ይጠ​ብቁ ዘንድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ዳዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሚ​ሄ​ድ​በት ቦታ ሁሉ ጠበ​ቀው።
15ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊ​ትም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው። 16የሦ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም የሠ​ራ​ዊት አለቃ ነበረ፤ የአ​ሒ​ሎ​ድም ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ፤ 17የአ​ኪ​ጦ​ብም ልጅ ሳዶቅ፥ የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም ልጅ አብ​ያ​ታር ካህ​ናት ነበሩ። አሳም ጸሓፊ ነበረ፤ 18የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያ​ስም አማ​ካሪ ነበረ፤ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና፥ ፊሊ​ታ​ው​ያን፥ የዳ​ዊ​ትም ልጆች የፍ​ርድ ቤት አለ​ቆች ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ