ነቢዩም ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፥ “ወገብህን ታጥቀህ ይህን የዘይት ቀንድ በእጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገለዓድም ሂድ። በዚያም በደረስህ ጊዜ የናሜሲን ልጅ የኢዮሣፍጥን ልጅ ኢዩን ታገኘዋለህ፤ ገብተህም ከወንድሞቹ መካከል አስነሣው፤ ወደ ጓዳም አግባው። የዘይቱንም ቀንድ ይዘህ በራሱ ላይ አፍስሰውና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ በለው፤ ከዚህም በኋላ በሩን ከፍተህ ሽሽ፥ አትዘግይም።” እንዲሁም ጐልማሳው ነቢይ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ሄደ። በገባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠራዊት አለቆች ተቀምጠው አገኘ፤ እርሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ የምናገረው መልእክት አለኝ” አለ። ኢዩም፥ “ከማንኛችን ጋር ነው?” አለ። እርሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ነው” አለ። ተነሥቶም ወደ ቤቱ ገባ፥ ዘይቱንም በራሱ ላይ አፍስሶ እንዲህ አለው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ። የባሪያዎቼን የነቢያትን ደም፥ የእግዚአብሔርንም ባሪያዎች ሁሉ ደም ከኤልዛቤል እጅና ከአክዓብ ቤት ሁሉ እጅ እበቀል ዘንድ የጌታህን የአክዓብን ቤት ታጠፋለህ።
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 9 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 9:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos