መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 7

7
1ኤል​ሳ​ዕም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነገ በዚህ ጊዜ በሰ​ማ​ርያ በር፥ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብስ በአ​ንድ ሰቅል አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄ​ትም በአ​ንድ ሰቅል ይሸ​መ​ታል” አለው። 2ንጉ​ሡም በእጁ ተደ​ግ​ፎት የሚ​ቆም የነ​በረ ያ ብላ​ቴና ለኤ​ል​ሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ የእ​ህል ሿሿቴ ቢያ​ደ​ርግ ይህ ነገር ይሆ​ና​ልን?” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እነሆ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታየ​ዋ​ለህ፤ ከዚያ ግን አት​ቀ​ም​ስም” አለ።
3በከ​ተ​ማ​ዋም በር አራት ለም​ጻ​ሞች ሰዎች ነበሩ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “እስ​ክ​ን​ሞት ድረስ በዚህ ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን? 4ወደ ከተማ ብን​ገባ ራብ በከ​ተማ አለና፥ በዚያ እን​ሞ​ታ​ለን፤ በዚ​ህም ብን​ቀ​መጥ እን​ሞ​ታ​ለን። እን​ግ​ዲህ ኑ፥ ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር እን​ሂድ፤ በሕ​ይ​ወት ቢያ​ኖ​ሩን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ቢገ​ድ​ሉ​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ተባ​ባሉ። 5በጨ​ለ​ማም ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ይሄዱ ዘንድ ተነሡ፤ ወደ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ሰፈር መጀ​መ​ሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ፥ እነሆ፥ በዚያ ማንም ሰው አል​ነ​በ​ረም። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሶ​ር​ያ​ው​ያን የሰ​ረ​ገላ ድምፅ፥ የፈ​ረስ ድም​ፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰ​ምቶአ​ቸ​ዋ​ልና፥ እርስ በር​ሳ​ቸው “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ይከ​ቡን ዘንድ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንና የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ነገ​ሥት ቀጥሮ አም​ጥ​ቶ​ብ​ናል” ይባ​ባሉ ነበር። 7ስለ​ዚ​ህም ተነ​ሥ​ተው በጨ​ለማ ሸሹ፤ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንና ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሰፈ​ሩን እን​ዳለ ትተው ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ያድኑ ዘንድ ሸሹ። 8እነ​ዚ​ያም ለም​ጻ​ሞች ወደ ሰፈሩ መጀ​መ​ሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ ወደ አንድ ድን​ኳን ገብ​ተው በሉ፤ ጠጡም፤ ከዚ​ያም ወር​ቅና ብር ልብ​ስም ወሰዱ፤ ሄደ​ውም ሸሸ​ጉት፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ወደ ሌላ ድን​ኳን ገቡ፤ ከዚ​ያም ደግሞ ወስ​ደው ሸሸጉ።
9ከዚ​ያም ወዲያ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “መል​ካም አላ​ደ​ረ​ግ​ንም፤ ዛሬ የመ​ል​ካም ምሥ​ራች ቀን ነው፤ እኛ ዝም ብለ​ናል፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ብን​ቆይ በደ​ለ​ኞች እን​ሆ​ና​ለን፤ ኑ፥ እን​ሂድ፤ ለን​ጉሥ ቤተ​ሰ​ብም እን​ና​ገር” ተባ​ባሉ። 10ገብ​ተ​ውም በከ​ተ​ማው በር ጮኹ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፥ “ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ገባን፤ እነ​ሆም፥ ፈረ​ሶ​ችና አህ​ዮች ታስ​ረው፥ ድን​ኳ​ኖ​ችም ተተ​ክ​ለው ነበር እንጂ ያገ​ኘ​ነው አል​ነ​በ​ረም፤ የሰ​ውም ድምፅ አል​ነ​በ​ረም።” 11የደ​ጁም ጠባ​ቂ​ዎች ለን​ጉሡ ይነ​ግሩ ዘንድ ወደ ውስጥ ገቡ፤ ለን​ጉ​ሡም ቤት አወሩ። 12ንጉ​ሡም በሌ​ሊት ተነ​ሥቶ ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ያደ​ረ​ጉ​ብ​ንን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ተራ​ብን ያው​ቃሉ፤ ስለ​ዚህ፦ ከከ​ተ​ማ​ይቱ በወጡ ጊዜ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው እን​ይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለን፤ ወደ ከተ​ማም እን​ገ​ባ​ለን ብለው በሜዳ ይሸ​ሸጉ ዘንድ ከሰ​ፈሩ ወጥ​ተ​ዋል” አላ​ቸው። 13ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እዚህ ከቀ​ሩት ፈረ​ሶች አም​ስት ይው​ሰዱ፤ እነሆ፥ እነ​ርሱ በቀ​ሩት በእ​ስ​ራ​ኤል ቍጥር ናቸው፥ እን​ስ​ደ​ድና ይዩ” አለ። 14ሁለት ፈረ​ሰ​ኞ​ች​ንም ወሰዱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም፥ “ሄዳ​ችሁ እዩ” ብሎ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን ንጉሥ ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ላከ። 15በኋ​ላ​ቸ​ውም እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ ተከ​ት​ለ​ዋ​ቸው ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ ሶር​ያ​ው​ያን ሲሸሹ የጣ​ሉት ልብ​ስና ዕቃ መን​ገ​ዱን ሁሉ ሞልቶ አገኙ። እነ​ዚያ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ተመ​ል​ሰው ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነገ​ሩት።
16ሕዝ​ቡም ወጥቶ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን ሰፈር በዘ​በዘ፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄት በአ​ንድ ሰቅል፥ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብ​ስም በአ​ንድ ሰቅል ተሸ​መተ። 17ንጉ​ሡም ያን እጁን ይደ​ግ​ፈው የነ​በ​ረ​ውን ብላ​ቴና በሩን ይጠ​ብቅ ዘንድ አቆ​መው። ሕዝ​ቡም በበሩ ረገ​ጠው፥ መል​እ​ክ​ተ​ኛው ወደ እርሱ በወ​ረደ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ተና​ገ​ረ​ውም ሞተ። 18ኤል​ሳ​ዕም ለን​ጉሡ፥ “ነገ በዚህ ጊዜ በሰ​ማ​ርያ በር ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብስ በአ​ንድ ሰቅል፥ አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄ​ትም በአ​ንድ ሰቅል፥ ይሸ​መ​ታል” ብሎ እንደ ተና​ገ​ረው ነገር እን​ዲሁ ሆነ። 19ያም ሎሌ ለኤ​ል​ሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ የእ​ህል ሿሿቴ ቢያ​ወ​ርድ ይህ ነገር ይሆ​ና​ልን?” ብሎ ነበር፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “እነሆ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታየ​ዋ​ለህ፥ ከዚ​ያም አት​ቀ​ም​ስም” ብሎት ነበር። 20እን​ዲ​ሁም ሆነ፤ ሕዝ​ቡም በበሩ ረገ​ጠ​ውና ሞተ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ