የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 3

3
በሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን መካ​ከል የተ​ደ​ረገ ጦር​ነት
1በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ክ​ዓብ ልጅ ኢዮ​ራም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ ዐሥራ ሁለ​ትም ዓመት ነገሠ። 2በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ነገር ግን እንደ አባ​ቱና እንደ እናቱ አል​ነ​በ​ረም፤ አባ​ቱም ያሠ​ራ​ውን የበ​ዓ​ልን ምስል አጠፋ። 3ነገር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያሳ​ታ​ቸ​ውን የና​ባ​ጥን ልጅ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ኀጢ​አት ተከ​ተለ፤ እር​ሱ​ንም አል​ተ​ወም።
4የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ ሞሳ ባለ በጎች ነበር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ መቶ ሺህ የጠ​ጕር አውራ በጎ​ች​ንና መቶ ሺህ ጠቦ​ቶ​ችን ይገ​ብ​ር​ለት#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “መቶ ሽህ ጠቦ​ቶ​ች​ንና የመቶ ሽህ አውራ በጎች ጠጕ​ርን” ይላል። ነበር። 5አክ​ዓ​ብም ከሞተ በኋላ የሞ​ዓብ ንጉሥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ከዳው። 6በዚ​ያም ጊዜ ንጉሡ ኢዮ​ራም ከሰ​ማ​ርያ ወጥቶ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው። 7ወደ ይሁ​ዳም ንጉሥ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ “የሞ​ዓብ ንጉሥ ከዳኝ፤ ከእኔ ጋር በሞ​ዓብ ላይ ለሰ​ልፍ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” ብሎ፤ ላከ። እር​ሱም፥ “እወ​ጣ​ለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ አን​ተም እንደ እኔ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶ​ቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለ። 8ደግ​ሞም፥ “በየ​ት​ኛው መን​ገድ እን​ሄ​ዳ​ለን?” አለ፤ እር​ሱም፥ “በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድረ በዳ መን​ገድ” አለው። 9የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ሄዱ፤ የሰ​ባ​ትም ቀን መን​ገድ ዞሩ፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱና ለሚ​ጫኑ እን​ስ​ሶች ውኃ አጡ። 10የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሞ​ዓብ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እነ​ዚ​ህን ሦስ​ቱን ነገ​ሥ​ታት ጠር​ቶ​አ​ልና ወዮ!” አለ። 11ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “በእ​ርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ን​ጠ​ይ​ቅ​በት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ በዚህ አይ​ገ​ኝ​ምን?” አለ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አገ​ል​ጋ​ዮች አንዱ፥ “ኤል​ያ​ስን እጁን ያስ​ታ​ጥብ የነ​በ​ረው የሣ​ፋጥ ልጅ ኤል​ሳዕ እዚህ አለ” ብሎ መለሰ። 12ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ርሱ ዘንድ ይገ​ኛል” አለ። የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ወደ እርሱ ወረዱ።
13ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባ​ትህ ነቢ​ያ​ትና ወደ እና​ትህ ነቢ​ያት ሂድ፥” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “አይ​ደ​ለም፤ በሞ​ዓብ እጅ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን ሦስት ነገ​ሥ​ታት ጠር​ቶ​አ​ልን?” አለው። 14ኤል​ሳ​ዕም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ያፈ​ርሁ ባል​ሆን ኖሮ አን​ተን ባል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ሁና ባላ​የሁ ነበር። 15አሁ​ንም ባለ በገና አም​ጡ​ልኝ” አለ። ባለ በገ​ና​ውም በደ​ረ​ደረ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ መጣ። 16እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድ​ጓድ ቈፍሩ። 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ ነፋስ አታ​ዩም፤ ዝና​ብም አታ​ዩም፤ ይህ ሸለቆ ግን ውኃ ይሞ​ላል፤ እና​ን​ተም፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም፥ እን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ሁም፥ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ። 18ይህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ቀላል ነገር ነውና፤ ደግ​ሞም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል። 19የተ​መ​ሸ​ጉ​ት​ንም ከተ​ሞች ሁሉ ትመ​ታ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ት​ንም ዛፎች ሁሉ ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ትደ​ፍ​ና​ላ​ችሁ፤ መል​ካ​ሞ​ቹ​ንም እር​ሻ​ዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ታበ​ላ​ሻ​ላ​ችሁ።” 20በነ​ጋ​ውም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ቀ​ር​ብ​በት ጊዜ፥ እነሆ፥ ውኃ በኤ​ዶ​ም​ያስ መን​ገድ መጣ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውኃ ሞላች።
21ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ሁሉ እነ​ዚያ ነገ​ሥ​ታት ሊወ​ጉ​አ​ቸው እንደ መጡ በሰሙ ጊዜ፥ “ሁላ​ችሁ መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ችን ይዛ​ችሁ ርዱን” ብለው በሀ​ገ​ራ​ቸው ሁሉ ጮኹ። ተሰ​በ​ሰ​ቡም፤ ወጥ​ተ​ውም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ ቆሙ። 22ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ ፀሐ​ይም በው​ኃው ላይ አን​ጸ​ባ​ረቀ፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም በፊ​ታ​ቸው ውኃው እንደ ደም ቀልቶ አዩና፦ 23“ይህ የጦር ደም ነው፤ እነ​ዚያ ነገ​ሥ​ታት እርስ በር​ሳ​ቸው ተጋ​ደሉ፤ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገደሉ፤ አሁ​ንም ሞዓብ ሆይ! እን​ግ​ዲህ ወደ ምር​ኮህ ሂድ” አሉ። 24ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር በመጡ ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ተነ​ሥ​ተው ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን መቱ፤ እነ​ር​ሱም ከፊ​ታ​ቸው ሸሹ፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንም እየ​መቱ ወደ ሀገሩ ውስጥ ገቡ። 25ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረሱ፤ በመ​ል​ካ​ሞ​ቹም እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ እስ​ኪ​ሞሉ ድረስ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው አንድ አንድ ድን​ጋይ ይጥል ነበር፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቅጥር አፈ​ረሱ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወን​ጭ​ፎ​ችም ከብ​በው መቱ​አ​ቸው። 26የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ እንደ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውና ድል እን​ደ​ነ​ሡ​አ​ቸው ባየ ጊዜ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰባት መቶ ሰዎ​ችን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ወደ ኤዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ ያልፉ ዘንድ ሞከሩ፤ አል​ቻ​ሉ​ምም። 27ከዚህ በኋላ በእ​ርሱ ፋንታ ንጉሥ የሚ​ሆ​ነ​ውን የበ​ኵር ልጁን ወስዶ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በቅ​ጥሩ ላይ አቀ​ረ​በው። እስ​ራ​ኤ​ልም ታላቅ ጸጸት ተጸ​ጸቱ፤ ከዚ​ያም ርቀው ወደ ምድ​ራ​ቸው ተመ​ለሱ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ