መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 2:9-10

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 2:9-10 አማ2000

ከተ​ሻ​ገ​ሩም በኋላ ኤል​ያስ ኤል​ሳ​ዕን፥ “ከአ​ንተ ሳል​ወ​ሰድ አደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ የም​ት​ሻ​ውን ለምን” አለው፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “መን​ፈ​ስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለ። ኤል​ያ​ስም፥ “አስ​ቸ​ጋሪ ነገር ለም​ነ​ሃል፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ዘንድ በተ​ወ​ሰ​ድሁ ጊዜ ብታ​የኝ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አለ​ዚያ ግን አይ​ሆ​ን​ል​ህም” አለው።