የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 11

11
የይ​ሁዳ ንግ​ሥት ጎቶ​ልያ
(2ዜ.መ. 22፥10—23፥15)
1የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ዘር ሁሉ አጠ​ፋች። 2የን​ጉሡ የኢ​ዮ​ራም ልጅ የአ​ካ​ዝ​ያስ እኅት ኢዮ​ሳ​ቡ​ሄም የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ ኢዮ​አ​ስን ከተ​ገ​ደ​ሉት ከን​ጉሡ ልጆች መካ​ከል ሰርቃ ወሰ​ደ​ችው፤ እር​ሱ​ንና ሞግ​ዚ​ቱ​ንም ወደ እል​ፍኝ ወሰ​ደች፤ ከጎ​ቶ​ል​ያም ሸሸ​ገ​ችው፤ አል​ገ​ደ​ሉ​ት​ምም። 3በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ስድ​ስት ዓመት ሸሸ​ገ​ችው። ጎቶ​ል​ያም በሀ​ገሩ ላይ ነገ​ሠች።
4በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ፥ በኮ​ራ​ው​ያ​ንና በዘ​በ​ኞች ላይ ያሉ​ትን የመቶ አለ​ቆች ወሰደ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ባ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አማ​ላ​ቸው፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አሳ​ያ​ቸው። 5እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እን​ዲህ አድ​ርጉ፤ በሰ​ን​በት ቀን ከም​ት​ገ​ቡት ከእ​ና​ንተ ከሦ​ስት አንዱ እጅ በበር ተቀ​ም​ጣ​ችሁ የን​ጉ​ሡን ቤት ዘብ ጠብቁ፤ 6ሌላ​ውም ከሦ​ስት አንዱ እጅ በሰ​ፊው መን​ገድ በበሩ በኩል ተቀ​መጡ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ውም እጅ ከዘ​በ​ኞች ቤት በኋላ ባለው በር ሁኑ፤ ቤቱ​ንም አጽ​ን​ታ​ችሁ ጠብቁ፤ 7ከእ​ና​ን​ተም በሰ​ን​በት ቀን የም​ት​ወ​ጡት ሁለቱ እጅ ንጉሥ ያለ​በ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ጠብቁ። 8ንጉ​ሡ​ንም በዙ​ሪ​ያው ክበ​ቡት፤ የጦር ዕቃ​ች​ሁም በእ​ጃ​ችሁ ይሁን፤ በሰ​ል​ፋ​ች​ሁም መካ​ከል የሚ​ገባ ይገ​ደል፤ ንጉ​ሡም በወ​ጣና በገባ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ሁኑ።”
9መቶ አለ​ቆ​ችም ብልሁ ዮዳሄ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ በሰ​ን​በት ይገቡ የነ​በ​ሩ​ትን፥ በሰ​ን​በ​ትም ይወጡ የነ​በ​ሩ​ትን ሰዎች ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ። 10ዮዳ​ሄም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን የን​ጉ​ሡን የዳ​ዊ​ትን ሰይ​ፍና ጦር ሁሉ ለመቶ አለ​ቆች ሰጣ​ቸው። 11ዘበ​ኞ​ቹም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የጦር ዕቃ​ቸ​ውን በእ​ጃ​ቸው ይዘው በን​ጉሡ ዙሪያ ከቤቱ ቀኝ እስከ ቤቱ ግራ ድረስ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በቤቱ አጠ​ገብ ቆሙ። 12የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አው​ጥቶ ዘው​ዱን ጫነ​በት፤ ምስ​ክ​ሩ​ንም ሰጠው፤ ቀብ​ቶም አነ​ገ​ሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” እያሉ በእ​ጃ​ቸው አጨ​በ​ጨቡ።
13ጎቶ​ል​ያም ሲሮጡ የሕ​ዝ​ቡን ድምፅ በሰ​ማች ጊዜ ወደ ሕዝቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገባች። 14እነ​ሆም፥ ንጉ​ሡን እንደ ተለ​መ​ደው በዓ​ምዱ አጠ​ገብ ቆሞ፥ ከን​ጉ​ሡም ጋር መዘ​ም​ራ​ንና መለ​ከ​ተ​ኞች ቆመው አየች፤ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎ​አ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር። ጎቶ​ል​ያም ልብ​ስ​ዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው፥ ዐመፅ ነው፥” ብላ ጮኸች። 15ካህ​ኑም ዮዳሄ በጭ​ፍ​ራው ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን የመቶ አለ​ቆች፥ “ወደ ሰልፉ መካ​ከል አው​ጡ​አት፤ የሚ​ከ​ተ​ላ​ት​ንም በሰ​ይፍ ግደ​ሉት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፤ ካህኑ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አት​ገ​ደል” ብሎ​አ​ልና። 16እር​ስ​ዋ​ንም ይዘው በን​ጉሡ ቤት አጠ​ገብ ወደ አለ ወደ ፈረ​ሶች መግ​ቢያ መን​ገድ ወሰ​ዱ​አት፤ በዚ​ያም ገደ​ሉ​አት።
ካህኑ ዮዳሄ ያደ​ረ​ገው ለውጥ
(2ዜ.መ. 23፥16-21)
17ዮዳ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በን​ጉሡ፥ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ ደግ​ሞም በን​ጉ​ሡና በሕ​ዝቡ መካ​ከል ቃል ኪዳን አደ​ረገ። 18የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበ​ሩት፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሱ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም አደ​ቀቁ፥ የበ​ዓ​ል​ንም ካህን ማታ​ንን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ገደ​ሉት። ካህኑ ዮዳ​ሄም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾመ። 19መቶ አለ​ቆ​ቹ​ንና ኮራ​ው​ያ​ንን፥ ዘበ​ኞ​ች​ንና የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ ሁሉ ወሰ​ዳ​ቸው፤ ንጉ​ሡ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አወ​ጣው፤ በዘ​በ​ኞ​ችም በር መን​ገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመ​ጡት፤ በነ​ገ​ሥ​ታ​ቱም ዙፋን አስ​ቀ​መ​ጡት። 20የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ደስ አላ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ፀጥ አለች። ጎቶ​ል​ያ​ንም በን​ጉሡ ቤት አጠ​ገብ በሰ​ይፍ ገደ​ሉ​አት። 21ኢዮ​አ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሰ​ባት ዓመት ልጅ ነበረ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ