የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 8:10-24

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 8:10-24 አማ2000

በዚ​ህም የሚ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁን እመ​ክ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይህን ከማ​ድ​ረ​ጋ​ችሁ በፊት ፈቅ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ከአ​ምና ጀም​ሮም ይህን ጀም​ራ​ች​ኋል። አሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ፈጽ​ሙም፤ መፍ​ቀድ ከመ​ሻት ነውና፤ ማድ​ረ​ግም ከማ​ግ​ኘት ነውና። ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም። በዚህ ወራት ተካ​ክ​ላ​ችሁ እን​ድ​ት​ኖሩ ነው እንጂ ሌላው እን​ዲ​ያ​ርፍ እና​ን​ተን የም​ና​ስ​ጨ​ንቅ አይ​ደ​ለም። ኑሮ​አ​ችሁ በሁሉ የተ​ካ​ከለ ይሆን ዘንድ፥ የእ​ና​ንተ ትርፍ የእ​ነ​ር​ሱን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና፥ የእ​ነ​ር​ሱም ትርፍ የእ​ና​ን​ተን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና። መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ብዙ ያለው አላ​ተ​ረ​ፈም፤ ጥቂት ያለ​ውም አላ​ጐ​ደ​ለም።” በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው። ልመ​ና​ች​ን​ንም ተቀ​ብሎ፥ ጨክኖ ወደ እና​ንተ ይመጣ ዘንድ ቸኵ​ሏል። ስለ ወን​ጌል ትም​ህ​ርት አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ ያመ​ሰ​ገ​ኑ​ትን ወን​ድ​ማ​ች​ን​ንም ከእ​ርሱ ጋር ልከ​ናል። ይህም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብ​ርና የእ​ኛን በጎ ፈቃድ ለማ​ሳ​የት በም​ና​ገ​ለ​ግ​ል​ባት በዚች ጸጋ ከእኛ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ተሾመ። ስለ​ም​ና​ገ​ለ​ግ​ለው ስለ​ዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እን​ዳ​ይ​ነ​ቅ​ፈን እን​ጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለን። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብቻ ያይ​ደለ፥ ነገር ግን በሰው ፊትም መል​ካ​ሙን ነገር እና​ስ​ባ​ለ​ንና። በብዙ የፈ​ተ​ን​ነ​ው​ንና በሁ​ሉም ነገር ትጉህ ሆኖ ያገ​ኘ​ነ​ውን አሁ​ንም በእ​ና​ንተ እጅግ ስለ​ሚ​ታ​መን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚ​ሆ​ነ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ንን ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ል​ካ​ለን። ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮኝ የሚ​ሠራ ጓደ​ኛዬ ነው፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ቢሆኑ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሐዋ​ር​ያት ናቸው። አሁ​ንም መዋ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ንና እኛም በእ​ና​ንተ የም​ን​መ​ካ​በ​ትን ሥራ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ፊት በግ​ልጥ አሳ​ዩ​አ​ቸው።