በዚህም የሚጠቅማችሁን እመክራችኋለሁ፤ ይህን ከማድረጋችሁ በፊት ፈቅዳችኋልና፤ ከአምና ጀምሮም ይህን ጀምራችኋል። አሁንም አድርጉ፤ ፈጽሙም፤ መፍቀድ ከመሻት ነውና፤ ማድረግም ከማግኘት ነውና። ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚቻለው መጠን ቢሰጥ ይመሰገናል፤ በማይቻለውም መጠን አይደለም። በዚህ ወራት ተካክላችሁ እንድትኖሩ ነው እንጂ ሌላው እንዲያርፍ እናንተን የምናስጨንቅ አይደለም። ኑሮአችሁ በሁሉ የተካከለ ይሆን ዘንድ፥ የእናንተ ትርፍ የእነርሱን ጕድለት ይመላልና፥ የእነርሱም ትርፍ የእናንተን ጕድለት ይመላልና። መጽሐፍ እንዳለ፥ “ብዙ ያለው አላተረፈም፤ ጥቂት ያለውም አላጐደለም።”
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 8 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 8
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 8:10-15
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች