የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8:10-15

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8:10-15 አማ05

በዚህ ጉዳይ ለእናንተ መልካም መስሎ የታየኝን ምክር እሰጣችኋለሁ፤ ባለፈው ዓመት ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ይህን ለማድረግ በመጀመሪያ የፈለጋችሁት እናንተ ነበራችሁ። ስለዚህ የመስጠት ፈቃደኛነታችሁ አሳብ በሥራ ላይ ውሎ ወደ ፍጻሜ እንዲደርስ ባላችሁ መጠን ያንን ያሰባችሁትን አሁን አድርጉ። ለመስጠት መልካም ፈቃድ ካለ የሰው ልግሥና ተቀባይነት የሚያገኘው ባለው መጠን ሲሰጥ እንጂ በሌለው መጠን ሲሰጥ አይደለም። ይህንንም ስል ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ እንጂ እናንተ በመስጠት ስትቸገሩ ሌሎች እንዲያርፉ ብዬ አይደለም። እናንተ በምትቸገሩበት ጊዜ የእነርሱ ሀብት ለእናንተ ችግር እንዲውል አሁን የእናንተ ሀብት ለእነርሱ ችግር ይዋል፤ በዚህ ዐይነት በመካከላችሁ እኩልነት ይኖራል። ይህም፦ “ብዙ የሰበሰበ አልተረፈለትም፤ ትንሽ የሰበሰበም አልጐደለበትም” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።