የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ ለእናንተ አፋችን የተከፈተ ነው፤ ልባችንም የሰፋ ነው። ከእናንተ የደረሰ ኀዘን በእኛ የለም፤ ከእኛም በእናንተ ላይ የደረሰ ኀዘን የለም፤ ነገር ግን በልባችሁ አዝናችኋል። ልጆች እንደ መሆናችሁ፥ ይህን እላችኋለሁ፤ ከእናንተ ላይ ስለሚገባኝ ብድራቴ እናንተ ፍቅራችሁን አስፉልኝ። ተጠራጣሪዎች አትሁኑ፤ ወደማያምኑ ሰዎች አንድነትም አትሂዱ፤ ጽድቅን ከኀጢአት ጋር አንድ የሚያደርጋት ማን ነው? ብርሃንንስ ከጨለማ ጋር የሚቀላቅል ማን ነው? ክርስቶስን ከቤልሆር ጋር አንድ የሚያደርገው ማን ነው? ወይስ ምእመናንን ከመናፍቃን ጋር አንድ ወገን የሚያደርጋቸው ማን ነው? የእግዚአብሔርን ታቦትስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው? የሕያው እግዚአብሔር ማደሪያዎች እኛ አይደለንምን? እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “እኔ በእነርሱ አድራለሁ፤ በመካከላቸውም እኖራለሁ፤ አምላካቸውም እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል።” ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ። አባት እሆናችኋለሁ፤ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትሆኑኛላችሁ አለ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር።”
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 6 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 6
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 6:11-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos