የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 6:11-18

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 6:11-18 አማ2000

የቆ​ሮ​ን​ቶስ ሰዎች ሆይ፥ ለእ​ና​ንተ አፋ​ችን የተ​ከ​ፈተ ነው፤ ልባ​ች​ንም የሰፋ ነው። ከእ​ና​ንተ የደ​ረሰ ኀዘን በእኛ የለም፤ ከእ​ኛም በእ​ና​ንተ ላይ የደ​ረሰ ኀዘን የለም፤ ነገር ግን በል​ባ​ችሁ አዝ​ና​ች​ኋል። ልጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ፥ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ ላይ ስለ​ሚ​ገ​ባኝ ብድ​ራቴ እና​ንተ ፍቅ​ራ​ች​ሁን አስ​ፉ​ልኝ። ተጠ​ራ​ጣ​ሪ​ዎች አት​ሁኑ፤ ወደ​ማ​ያ​ምኑ ሰዎች አን​ድ​ነ​ትም አት​ሂዱ፤ ጽድ​ቅን ከኀ​ጢ​አት ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት ማን ነው? ብር​ሃ​ን​ንስ ከጨ​ለማ ጋር የሚ​ቀ​ላ​ቅል ማን ነው? ክር​ስ​ቶ​ስን ከቤ​ል​ሆር ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ማን ነው? ወይስ ምእ​መ​ና​ንን ከመ​ና​ፍ​ቃን ጋር አንድ ወገን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ማን ነው? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦ​ትስ በጣ​ዖት ቤት ውስጥ የሚ​ያ​ኖር ማን ነው? የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እኛ አይ​ደ​ለ​ን​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “እኔ በእ​ነ​ርሱ አድ​ራ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል።” ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ። አባት እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ አለ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}