የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 6:1-10

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 6:1-10 አማ2000

ከእ​ር​ሱም ጋር አብ​ረን እየ​ሠ​ራን፥ የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጓት እን​ማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለን። እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ሰማ​ሁህ፤ በመ​ዳ​ንም ቀን ረዳ​ሁህ” እነሆ፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ዛሬ ናት። አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ንም እን​ዳ​ይ​ነ​ቀፍ፥ በአ​ን​ዳች ነገር ማሰ​ና​ከያ እን​ዳ​ን​ሰጥ እን​ጠ​ን​ቀቅ። ነገር ግን በሁሉ ራሳ​ች​ንን አቅ​ን​ተን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን፤ በብዙ ትዕ​ግ​ሥ​ትና በመ​ከራ፥ በች​ግ​ርና በጭ​ን​ቀት ሁሉ፥ በመ​ገ​ረ​ፍና በመ​ታ​ሰር፥ በድ​ካ​ምና በመ​ታ​ወክ፥ በመ​ት​ጋ​ትና በመ​ጾም፥ በን​ጽ​ሕ​ናና በዕ​ው​ቀት፥ በም​ክ​ርና በመ​ታ​ገሥ፥ በቸ​ር​ነ​ትና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ አድ​ልዎ በሌ​ለ​በት ፍቅር፥ በእ​ው​ነት ቃል፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ለቀ​ኝና ለግራ በሚ​ሆን የጽ​ድቅ የጦር ዕቃ፥ በክ​ብ​ርና በው​ር​ደት፥ በም​ር​ቃ​ትና በር​ግ​ማን፥ እንደ አሳ​ቾች ስን​ታይ እው​ነ​ተ​ኞች ነን። እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቁ ስን​ታይ የታ​ወ​ቅን ነን፤ እንደ ሰነ​ፎች ስን​ታ​ይም ልባ​ሞች ነን፤ እንደ ሙታን ስን​ታይ ሕያ​ዋን ነን፤ የተ​ቀ​ጣን ስን​ሆ​ንም አን​ገ​ደ​ልም። ኀዘ​ን​ተ​ኞች ስን​ሆን ዘወ​ትር ደስ​ተ​ኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስን​ሆን ብዙ​ዎ​ችን እና​በ​ለ​ጽ​ጋ​ለን፤ ምንም የሌ​ለን ስን​ሆን ሁሉ በእ​ጃ​ችን ነው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}