ለክርስቶስም ወንጌል ጢሮአዳ በደረስሁ ጊዜ በእግዚአብሔር በሩ ተከፈተልኝ። ወንድሜን ቲቶን ስላላገኘሁት ለሰውነቴ ዕረፍት አላገኘሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ ተለይች ወደ መቄዶንያ ሄድሁ። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ድል በመንሣቱ የሚጠብቀን፥ በየሀገሩም ሁሉ የዕውቀቱን መዓዛ በእኛ የሚገልጥ እግዚአብሔር ይመስገን። በሚድኑትና በሚጠፉት ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ እኛ ነንና። የሞት መዓዛ የሚገባቸው ለሞት፥ የሕይወት መዓዛ የሚገባቸውም ለሕይወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚገባው ማነው? የእግዚአብሔርን ቃል በሌላ ቀላቅለው እንደሚሸቅጡ እንደ ብዙዎች አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላከ በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ እንናገራለን።
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 2 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 2
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 2:12-17
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos