የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 2:12-17

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 2:12-17 አማ2000

ለክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ጢሮ​አዳ በደ​ረ​ስሁ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሩ ተከ​ፈ​ተ​ልኝ። ወን​ድ​ሜን ቲቶን ስላ​ላ​ገ​ኘ​ሁት ለሰ​ው​ነቴ ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ተለ​ይች ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄድሁ። በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘወ​ትር ድል በመ​ን​ሣቱ የሚ​ጠ​ብ​ቀን፥ በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ የዕ​ው​ቀ​ቱን መዓዛ በእኛ የሚ​ገ​ልጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን። በሚ​ድ​ኑ​ትና በሚ​ጠ​ፉት ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ር​ስ​ቶስ መዓዛ እኛ ነንና። የሞት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸው ለሞት፥ የሕ​ይ​ወት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ለሕ​ይ​ወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚ​ገ​ባው ማነው? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በሌላ ቀላ​ቅ​ለው እን​ደ​ሚ​ሸ​ቅጡ እንደ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምና፤ በቅ​ን​ነት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተላከ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ና​ገ​ራ​ለን።