እንግዲህ እያዘንሁ ወደ እናንተ እንዳልመጣ በልቤ ይህን ወሰንሁ። እኔ ካሳዘንኋችሁማ እኔ ካሳዘንሁት በቀር ማን ደስ ያሰኘኛል? የእኔ ደስታ የሁላችሁ እንደ ሆነ በሁላችሁ አምኛለሁና በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ ከሚገባቸው ኀዘን እንዳያገኘኝ ይህን ጻፍሁላችሁ። ከብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት የተነሣ በብዙ እንባ ይህን ጽፌላችኋለሁ፤ ነገር ግን እጅግ እንደምወዳችሁ እንድታውቁ ነው እንጂ እንድታዝኑ አይደለም።
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 2 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 2
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 2:1-4
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos