እንግዲህ እናንተን እንዳላሳዝናችሁ በማሰብ ለጒብኝት ወደ እናንተ ተመልሼ ላለመምጣት ቊርጥ ውሳኔ አደረግሁ። ምንም እንኳ እናንተን ባሳዝናችሁ ካሳዘንኳችሁ ከእናንተ በስተቀር እኔን የሚያስደስት ማን ነው? እንደዚያ የጻፍኩላችሁም ወደ እናንተ ስመጣ ደስ ሊያሰኙኝ የሚገባቸው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ ብዬ ነው፤ የእኔ ደስታ የሁላችሁም ደስታ መሆኑን አምናለሁ። በትልቅ ሐዘንና በልብ ጭንቀት፥ በብዙ እንባም ሆኜ የጻፍኩላችሁ በጣም የምወዳችሁ መሆኔን እንድታውቁ ብዬ ነው እንጂ ላሳዝናችሁ ብዬ አይደለም።
2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:1-4
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos