መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 17

17
የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ ዘመነ መን​ግ​ሥት
1ከአ​ሳም በኋላ ልጁ ኢዮ​ሳ​ፍጥ ነገሠ፤ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠነ​ከረ። 2በተ​መ​ሸ​ጉ​ትም በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ሠራ​ዊ​ቱን አኖረ፤ በይ​ሁ​ዳም ሀገር፥ አባ​ቱም አሳ በወ​ሰ​ዳ​ቸው በኤ​ፍ​ሬም ከተ​ሞች መሳ​ፍ​ን​ቱን አስ​ቀ​መጠ። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ ጋር ነበረ፤ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም በአ​ባቱ በዳ​ዊት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በዳ​ዊት” አይ​ልም። መን​ገድ ሄዶ​አ​ልና፥ ጣዖ​ት​ንም አል​ፈ​ለ​ገ​ምና፤ 4ነገር ግን የአ​ባ​ቱን አም​ላክ ፈለገ፤ በአ​ባ​ቱም ትእ​ዛዝ ሄደ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥራ አይ​ደ​ለም። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ቱን በእጁ አጸና፤ ይሁ​ዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ አመጣ፤ እጅ​ግም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ሆነ​ለት። 6ልቡም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ ከፍ ከፍ አለ፤ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችና የማ​ም​ለ​ኪያ አፀ​ዱ​ንም ከይ​ሁዳ አስ​ወ​ገደ።
7በነ​ገ​ሠም በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና ኀያ​ላ​ኑን ሰዎች አብ​ድ​ያ​ስን፥ ዘካ​ር​ያ​ስን፥ ናት​ና​ኤ​ልን፥ ሚኪ​ያ​ስን ላከ። 8ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያ​ንን ሸማ​ያን፥ ነታ​ን​ያን፥ ዛባ​ድ​ያን፥ አሣ​ሄ​ልን፥ ሰሚ​ራ​ሞ​ትን፥ ዮና​ታ​ንን፥ አዶ​ን​ያ​ስን፥ ጦብ​ያን፥ ጦባ​ዶ​ን​ያ​ስን#“ጦባ​ዶ​ን​ያን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ካህ​ና​ቱን ኤሊ​ሳ​ማ​ንና ኢዮ​ራ​ምን ላከ። 9እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ይዘው በይ​ሁዳ ያስ​ተ​ምሩ ነበር፤ ወደ ይሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ተመ​ላ​ል​ሰው ሕዝ​ቡን አስ​ተ​ማሩ።
10በይ​ሁ​ዳም ዙሪያ በነ​በሩ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ድን​ጋጤ ሆነ፤ ከኢ​ዮ​ሳ​ፍ​ጥም ጋር አል​ተ​ዋ​ጉም። 11ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ እጅ መን​ሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንም ደግሞ ከመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎ​ች​ንና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየ​ሎ​ችን#“ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየ​ሎች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ያመ​ጡ​ለት ነበር። 12ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እየ​በ​ረ​ታና እጅ​ግም እየ​ከ​በረ ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ግን​ቦ​ች​ንና የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችን#ዕብ. “የጎ​ተራ ከተ​ሞ​ችን” ይላል። ሠራ። 13በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ብዙ ሥራ ሠራ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ነበ​ሩት። 14ቍጥ​ራ​ቸ​ውም እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ይህ ነበረ፤ ከይ​ሁዳ ሻለ​ቆች አለ​ቃው ዓድ​ናስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ፤ 15ከእ​ር​ሱም በኋላ አለ​ቃው ኢዮ​አ​ናን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ 16ከእ​ር​ሱም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግል የዝ​ክሪ ልጅ ማስ​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ። 17ከብ​ን​ያ​ምም ጽኑዕ ኀያል የነ​በ​ረው ኤሊ​ያዳ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ቀስት የሚ​ገ​ትሩ፥ ወን​ጭፍ የሚ​ወ​ነ​ጭፉ ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ 18ከእ​ር​ሱም በኋላ ዮዛ​ባድ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ለሰ​ልፍ የተ​ዘ​ጋጁ መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ። 19ንጉሡ በተ​መ​ሸጉ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ካኖ​ራ​ቸ​ውም ሌላ እነ​ዚህ ንጉ​ሡን ያገ​ለ​ግሉ ነበር።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ