የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 25:1-22

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 25:1-22 አማ2000

ሳሙ​ኤ​ልም ሞተ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ በአ​ር​ማ​ቴ​ምም በቤቱ ቀበ​ሩት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ። በማ​ዖ​ንም የተ​ቀ​መጠ አንድ ሰው ነበረ፤ ከብ​ቱም በቀ​ር​ሜ​ሎስ ነበረ፤ እጅ​ግም ታላቅ ሰው ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም ሦስት ሺህ በጎ​ችና አንድ ሺህ ፍየ​ሎች ነበ​ሩት፤ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም በጎ​ቹን ሊሸ​ልት ሄደ። የሰ​ው​ዬ​ውም ስም ናባል፥ የሚ​ስ​ቱም ስም አቤ​ግያ ነበረ፤ ሴቲ​ቱም ደግና ብልህ፥ መል​ክ​ዋም እጅግ የተ​ዋበ ነበረ፤ ሰው​ዬው ግን ጨካ​ኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብ​ሩም ክፉ ነበረ። ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ ሳለ፥ “ናባል በቀ​ር​ሜ​ሎስ በጎ​ቹን ይሸ​ል​ታል” የሚል ወሬ ሰማ። ዳዊ​ትም ዐሥር ብላ​ቴ​ኖ​ችን ላከ፤ ለብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አለ፥ “ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወጥ​ታ​ችሁ ወደ ናባል ሂዱ፤ በስ​ሜም ሰላም በሉት፤ እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ደኅ​ን​ነ​ትና ሰላም ለአ​ን​ተና ለቤ​ትህ፥ ለአ​ን​ተም ለሆ​ኑት ሁሉ ይሁን። አሁ​ንም በጎ​ችህ እን​ደ​ሚ​ሸ​ለቱ ከእኛ ጋር በም​ድረ በዳ ያሉ ሰዎች ነገ​ሩን፤ እኛም አል​ከ​ለ​ከ​ል​ና​ቸ​ውም፤ በቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም በነ​በ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ከመ​ን​ጋ​ቸው ይሰ​ጡን ዘንድ አላ​ዘ​ዝ​ና​ቸ​ውም። ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን ጠይ​ቃ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ይነ​ግ​ሩ​ሃል፤ አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ በመ​ል​ካም ቀን መጥ​ተ​ና​ልና ብላ​ቴ​ኖች በፊ​ትህ ሞገስ ያግኙ፤ በእ​ጅ​ህም ከተ​ገ​ኘው ለል​ጅህ ለዳ​ዊት እባ​ክህ፥ ላክ።” የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች መጡ፤ ይህ​ንም የላ​ካ​ቸ​ውን ቃል ሁሉ በዳ​ዊት ስም ለና​ባል ነገ​ሩት፤ ናባ​ልም ተነ​ሥቶ ለዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእ​ሴ​ይስ ልጅ ማን ነው? እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከጌ​ቶ​ቻ​ቸው የኰ​በ​ለሉ አገ​ል​ጋ​ዮች ዛሬ ብዙ ናቸው። እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና የወ​ይን ጠጄን፥ ለሸ​ላ​ቾ​ቼም ያረ​ድ​ሁ​ትን ሥጋ ወስጄ ከወ​ዴት እንደ ሆኑ ለማ​ላ​ው​ቃ​ቸው ሰዎች እሰ​ጣ​ለ​ሁን?” የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ዞረው በመ​ጡ​በት መን​ገድ ተመ​ለሱ፤ መጥ​ተ​ውም ይህን ነገር ሁሉ ለዳ​ዊት ነገ​ሩት። ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “ሁላ​ችሁ ሰይ​ፋ​ች​ሁን ታጠቁ” አላ​ቸው። ሁሉም ሰይ​ፋ​ቸ​ውን ታጠቁ፤ ዳዊ​ትም ሰይ​ፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ዳዊ​ትን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ሁለት መቶ​ውም በጓ​ዛ​ቸው ዘንድ ተቀ​መጡ። ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ ለና​ባል ሚስት ለአ​ቤ​ግያ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በም​ድረ በዳ ሳለ ጌታ​ች​ንን ሰላም ሊሉት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እርሱ ግን ፊቱን አዞ​ረ​ባ​ቸው። እነ​ዚህ ሰዎች ግን በእኛ ዘንድ እጅግ ደጎች ነበሩ፤ የከ​ለ​ከ​ሉ​ንም የለም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር በኖ​ር​ን​በት ዘመን ሁሉ በም​ድረ በዳ ሳለን ከመ​ን​ጋው እን​ሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ያዘ​ዙን አን​ዳች ነገር የለም። ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሆነን መን​ጋ​ውን በጠ​በ​ቅ​ን​በት ዘመን ሁሉ በም​ድረ በዳ ሌሊ​ትና ቀን አጥር ሆነ​ውን ነበር። ስለ​ዚ​ህም በጌ​ታ​ች​ንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እን​ዲ​መጣ ተቈ​ር​ጦ​አ​ልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊና​ገ​ረው አይ​ች​ል​ምና የም​ታ​ደ​ር​ጊ​ውን ተመ​ል​ከ​ቺና ዕወቂ።” አቤ​ግ​ያም ፈጥና፦ ሁለት መቶ እን​ጀራ፥ ሁለት አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ፥ አም​ስት የተ​ዘ​ጋጁ በጎች፥ አም​ስ​ትም መስ​ፈ​ሪያ በሶ፥ አንድ ጎሞር ዘቢብ፥ ሁለት መቶም የበ​ለስ ጥፍ​ጥፍ ወሰ​ደች፥ በአ​ህ​ዮ​ችም ላይ አስ​ጫ​ነች። ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ዋም፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ በፊቴ ሂዱ፤ እነ​ሆም እከ​ተ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አለች። ይህ​ንም ለባ​ልዋ ለና​ባል አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም። እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ተቀ​ምጣ በተ​ራ​ራው ላይ በተ​ሰ​ወረ ስፍራ በወ​ረ​ደች ጊዜ፥ እነሆ፥ ዳዊ​ትና ሰዎቹ ወደ እር​ስዋ ወር​ደው ተቀ​በ​ሏት፤ እር​ስ​ዋም ተገ​ና​ኘ​ቻ​ቸው። ዳዊ​ትም አለ፥ “ለዚህ ሰው ከሆ​ነው ሁሉ አንድ ነገር እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​በት በእ​ው​ነት ከብ​ቱን ሁሉ በም​ድረ በዳ በከ​ንቱ ጠበ​ቅሁ፤ ከገ​ን​ዘቡ ሁሉ አን​ዳች ይወ​ስ​ዱ​በት ዘንድ ያዘ​ዝ​ነው የለም፤ እር​ሱም በበጎ ፋንታ ክፉ መለ​ሰ​ልኝ። ለና​ባ​ልም ከሆ​ነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አጥር ተጠ​ግቶ የሚ​ሸን አንድ ስንኳ ብን​ተው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዳ​ዊት ላይ እን​ዲህ ያድ​ርግ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ምር” ብሎ ነበር።