የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 24:1-7

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 24:1-7 አማ2000

ዳዊ​ትም ከዚያ መጥቶ በዓ​ይን ጋዲ በጠ​ባብ ቦታ ተቀ​መጠ፤ ሳኦ​ልም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከማ​ሳ​ደድ ከተ​መ​ለሰ በኋላ፥ “እነሆ! ዳዊት በዓ​ይን ጋዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገ​ሩት። ሳኦ​ልም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ለመ​ፈ​ለግ ዋሊ​ያ​ዎች ወደ​ሚ​ታ​ደ​ኑ​ባ​ቸው ዓለ​ቶች ሄደ። በመ​ን​ገ​ድም አጠ​ገብ ወዳ​ሉት የበ​ጎች ማደ​ሪ​ያ​ዎች ወጣ፤ በዚ​ያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ወገ​ቡን ይሞ​ክር ዘንድ ወደ​ዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ከዋ​ሻው በው​ስ​ጠ​ኛው ቦታ ተቀ​ም​ጠው ነበር። የዳ​ዊ​ትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ ጠላ​ት​ህን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ን​ህም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረህ ቀን እነሆ ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ የሳ​ኦ​ልን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ዘርፍ በቀ​ስታ ቈረጠ። ከዚ​ያም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የሳ​ኦ​ልን የል​ብ​ሱን ዘርፍ ስለ ቈረጠ የዳ​ዊት ልብ በኀ​ዘን ተመታ። ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባው ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው በጌ​ታዬ ላይ እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር አደ​ርግ ዘንድ፥ እጄ​ንም እጥ​ል​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው” አላ​ቸው።