የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 24

24
ዳዊት በሳ​ኦል ላይ ያደ​ረ​ገው ርኅ​ራኄ
1ዳዊ​ትም ከዚያ መጥቶ በዓ​ይን ጋዲ በጠ​ባብ ቦታ ተቀ​መጠ፤ 2ሳኦ​ልም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከማ​ሳ​ደድ ከተ​መ​ለሰ በኋላ፥ “እነሆ! ዳዊት በዓ​ይን ጋዲ ምድረ በዳ አለ” ብለው ነገ​ሩት። 3ሳኦ​ልም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ለመ​ፈ​ለግ ዋሊ​ያ​ዎች ወደ​ሚ​ታ​ደ​ኑ​ባ​ቸው ዓለ​ቶች ሄደ። 4በመ​ን​ገ​ድም አጠ​ገብ ወዳ​ሉት የበ​ጎች ማደ​ሪ​ያ​ዎች ወጣ፤ በዚ​ያም ዋሻ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ወገ​ቡን ይሞ​ክር ዘንድ ወደ​ዚያ ዋሻ ገባ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ከዋ​ሻው በው​ስ​ጠ​ኛው ቦታ ተቀ​ም​ጠው ነበር። 5የዳ​ዊ​ትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ ጠላ​ት​ህን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ን​ህም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረህ ቀን እነሆ ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ የሳ​ኦ​ልን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ዘርፍ በቀ​ስታ ቈረጠ። 6ከዚ​ያም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የሳ​ኦ​ልን የል​ብ​ሱን ዘርፍ ስለ ቈረጠ የዳ​ዊት ልብ በኀ​ዘን ተመታ። 7ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባው ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው በጌ​ታዬ ላይ እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር አደ​ርግ ዘንድ፥ እጄ​ንም እጥ​ል​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው” አላ​ቸው። 8ዳዊ​ትም በዚህ ቃል ሰዎ​ቹን ከለ​ከ​ላ​ቸው። በሳ​ኦ​ልም ላይ ተነ​ሥ​ተው ይገድ​ሉት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸ​ውም፤ ሳኦ​ልም ከዋ​ሻው ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ።
9ከእ​ር​ሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፤ ከዋ​ሻ​ውም ወጣ፤ ከሳ​ኦ​ልም በኋላ፦“ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጮኸ፤ ሳኦ​ልም ወደ ኋላው ተመ​ለ​ከተ፤ ዳዊ​ትም ወደ ምድር ተጐ​ን​ብሶ እጅ ነሣ። 10ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን አለው፥ “እነሆ፥ ዳዊት ክፉ ነገር ይሻ​ብ​ሃል የሚ​ሉ​ህን ሰዎች ቃል ለምን ትሰ​ማ​ለህ? 11እነሆ፥ ዛሬ በዋ​ሻው ውስጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ እንደ ሰጠህ ዐይ​ንህ አይ​ታ​ለች፤ አን​ተ​ንም እን​ድ​ገ​ድ​ልህ ሰዎች ተና​ገ​ሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ ነውና እጄን በጌ​ታዬ ላይ አል​ዘ​ረ​ጋም ብዬ ራራ​ሁ​ልህ። 12እነሆ፥ የል​ብ​ስህ ዘርፍ በእጄ እን​ዳለ ተመ​ል​ክ​ተህ ዕወቅ፤ የል​ብ​ስ​ህ​ንም ዘርፍ በቈ​ረ​ጥሁ ጊዜ አል​ገ​ደ​ል​ሁ​ህም፤ ስለ​ዚ​ህም በእጄ ክፋት፥ በደ​ልና ክዳት እን​ደ​ሌለ፥ አን​ተ​ንም እን​ዳ​ል​በ​ደ​ል​ሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍ​ሴን ልታ​ጠፋ ታጠ​ም​ዳ​ለህ። 13እግ​ዚ​እ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን ይበ​ቀ​ል​ልኝ፤ እጄ ግን በአ​ንተ ላይ አት​ሆ​ንም። 14የጥ​ንት ምሳሌ፦ ‘ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ኀጢ​አት ይወ​ጣል’ እን​ደ​ሚል፥ እጄ ግን በአ​ንተ ላይ አት​ሆ​ንም። 15አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማንን ለማ​ሳ​ደድ ወጥ​ተ​ሀል? አን​ተስ ማንን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ? የሞተ ውሻን ታሳ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ወይስ ቍን​ጫን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ? 16እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዳኛ ይሁን፤ በእ​ኔና በአ​ን​ተም መካ​ከል ይፍ​ረድ፤ አይ​ቶም ለእኔ ይፍ​ረድ፤ ከእ​ጅ​ህም ያድ​ነኝ።”
17እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ይህን ቃል ለሳ​ኦል መን​ገር በፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለ፤ ሳኦ​ልም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ። 18ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን አለው፥ “እኔ ክፉ በመ​ለ​ስ​ሁ​ልህ ፋንታ በጎ መል​ሰ​ህ​ል​ኛ​ልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዛሬ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶኝ ሳለ አል​ገ​ደ​ል​ኸ​ኝ​ምና ለእኔ መል​ካም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ኽ​ልኝ ለእኔ ነገ​ር​ኸኝ። 20ጠላ​ቱን ተቸ​ግሮ አግ​ኝቶ በመ​ል​ካም መን​ገድ ሸኝቶ የሚ​ሰ​ድድ ማን ነው? ስለ​ዚህ ለእኔ ስላ​ደ​ረ​ግ​ኸው ቸር​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሙን ይመ​ል​ስ​ልህ። 21አሁ​ንም እነሆ፥ አንተ በር​ግጥ ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መን​ግ​ሥት በእ​ጅህ እን​ድ​ት​ጸና እኔ አው​ቃ​ለሁ። 22አሁን እን​ግ​ዲህ ከእኔ በኋላ ዘሬን እን​ዳ​ት​ነ​ቅል ከአ​ባ​ቴም ቤት ስሜን እን​ዳ​ታ​ጠ​ፋው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማል​ልኝ።” 23ዳዊ​ትም ለሳ​ኦል ማለ​ለት፤ ሳኦ​ልም ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወደ ጠባቡ ወደ ሜሴራ ወጡ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ