የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:32-49

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:32-49 አማ2000

ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ስለ እርሱ የማ​ንም ልብ አይ​ው​ደቅ፤ እኔ ባሪ​ያህ ሄጄ ያን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እወ​ጋ​ዋ​ለሁ” አለው። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “አንተ ገና ብላ​ቴና ነህና፥ እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ን​ነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለመ​ው​ጋት ትሄድ ዘንድ አት​ች​ልም” አለው። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን አለው፥ “እኔ ባሪ​ያህ የአ​ባ​ቴን በጎች ስጠ​ብቅ አን​በሳ ወይም ድብ ይመጣ ነበር፤ ከመ​ን​ጋ​ውም ጠቦት ይወ​ስድ ነበር። በኋ​ላ​ውም እከ​ተ​ለ​ውና እመ​ታው ነበር። ከአ​ፉም አስ​ጥ​ለው ነበር፤ በተ​ነ​ሣ​ብ​ኝም ጊዜ ጕሮ​ሮ​ውን አንቄ እመ​ታ​ውና እገ​ድ​ለው ነበር። እኔ ባሪ​ያህ አን​በ​ሳና ድብ ገደ​ልሁ፤ ይህም ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ከእ​ነ​ርሱ እንደ አንዱ ይሆ​ናል። እን​ግ​ዲህ እገ​ድ​ለው ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን አስ​ወ​ግድ ዘንድ ዛሬ አል​ሄ​ድ​ምን? የሕ​ያው አም​ላክ ጭፍ​ሮ​ችን ይገ​ዳ​ደር ዘንድ ይህ ቈላፍ ምን​ድን ነው?” ዳዊ​ትም፥ “ከአ​ን​በ​ሳና ከድብ እጅ ያስ​ጣ​ለኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እጅ ያስ​ጥ​ለ​ኛል” አለ። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን” አለው። ሳኦ​ልም ለዳ​ዊት ጥሩር አለ​በ​ሰው፤ በራ​ሱም ላይ የናስ ቍር ደፋ​ለት። ዳዊ​ት​ንም ሰይ​ፉን በል​ብሱ ላይ አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ ዳዊ​ትም አን​ድና ሁለት ጊዜ ሲራ​መድ ደከመ። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “አለ​መ​ድ​ሁ​ምና በዚህ መሄድ አል​ች​ልም” አለው። ከላ​ዩም አወ​ለ​ቁ​ለት። ዳዊ​ትም በት​ሩን በእጁ ያዘ፤ ከወ​ን​ዝም አም​ስት ድብ​ል​ብል ድን​ጋ​ዮ​ችን መረጠ፤ በእ​ረኛ ኮሮ​ጆ​ውም በኪሱ ከተ​ታ​ቸው፤ ወን​ጭ​ፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ቀረበ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በፊቱ ይሄድ ነበር። ጎል​ያ​ድም ዳዊ​ትን ትኩር ብሎ አየው፤ ቀይ ብላ​ቴና፥ መል​ኩም ያማረ ነበ​ረና ናቀው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ወደ እኔ ና፤ ሥጋ​ህ​ንም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው። ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን አለው፥ “አንተ ሰይ​ፍና ጦር፥ ጋሻም ይዘህ ትመ​ጣ​ብ​ኛ​ለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው በእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍ​ሮች አም​ላክ ስም በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ አን​ተን በእጄ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ እመ​ታ​ህ​ማ​ለሁ፤ ራስ​ህ​ንም ከአ​ንተ እቈ​ር​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ሬሳ​ህ​ንና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሬሶች ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት ዛሬ እሰ​ጣ​ለሁ። ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር እን​ዳለ ያው​ቃሉ፤ ይህም ጉባኤ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ይ​ፍና በጦር የሚ​ያ​ድን እን​ዳ​ይ​ደለ ያው​ቃል። ሰልፉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ን​ተን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።” ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ተነ​ሥቶ ዳዊ​ትን ሊገ​ና​ኘው በቀ​ረበ ጊዜ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ሊገ​ና​ኘው ወደ ሰልፉ ሮጠ። ዳዊ​ትም እጁን ወደ ኮሮ​ጆው አግ​ብቶ አንድ ድን​ጋይ ወሰደ፤ ወነ​ጨ​ፈ​ውም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ግን​ባ​ሩን መታው፤ ድን​ጋ​ዩም ጥሩ​ሩን ዘልቆ በግ​ን​ባሩ ተቀ​ረ​ቀረ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ በፊቱ ተደፋ።