መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:28-30

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:28-30 አማ2000

ታላቅ ወን​ድ​ሙም ኤል​ያብ ከሰ​ዎች ጋር ሲነ​ጋ​ገር ሰማ፤ ኤል​ያ​ብም በዳ​ዊት ላይ እጅግ ተቈጣ፥ “ለምን ወደ​ዚህ ወረ​ድህ? እነ​ዚ​ያ​ንስ ጥቂ​ቶች በጎች በም​ድረ በዳ ለማን ተው​ሃ​ቸው? እኔ ኵራ​ት​ህ​ንና የል​ብ​ህን ክፋት አው​ቃ​ለ​ሁና ሰል​ፉን ለማ​የት መጥ​ተ​ሃል” አለው። ዳዊ​ትም፥ “እኔ ምን አደ​ረ​ግሁ? ይህ ታላቅ ነገር አይ​ደ​ለ​ምን?” አለ። ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ወደ ሌላ ሰው ዘወር አለ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ያለ ነገር ተና​ገረ፤ ሕዝ​ቡም እንደ ቀድ​ሞው ያለ ነገር መለ​ሱ​ለት።