አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:28-30

አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 17:28-30 አማ05

የዳዊት ታላቅ ወንድም ኤሊአብም ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር ሰማ፤ እርሱም በዳዊት ላይ በጣም ተቈጥቶ “እዚህ ምን ትሠራለህ? በበረሓ ያሉትንስ እነዚያን ጥቂቶች በጎችህን ለማን ተውካቸው? እኔ ትዕቢተኛነትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ! አሁን የመጣኸው እኮ የጦርነቱን ሁኔታ ለመመልከት ነው!” አለው። ዳዊትም “አሁን እኔ ምን አደረግሁ? ለመጠየቅ እንኳ አልችልምን?” ሲል መለሰለት፤ ከዚያም ወደ ሌላው ሰው መለስ ብሎ ያንኑ ጥያቄ አቀረበለት፤ በጠየቀ ቊጥር የሚያገኘው መልስ ተመሳሳይ ነበር።