የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 15

15
ሳኦል ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ጋር ያደ​ረ​ገው ጦር​ነት
1ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን አለው፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን እቀ​ባህ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከኝ፤ አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ። 2የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ በመ​ን​ገድ እንደ ተዋጉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ክፉ ያደ​ረ​ጉ​ትን አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ዛሬ እበ​ቀ​ላ​ለሁ። 3አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”
4ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን ጠርቶ በጌ​ል​ጌላ ቈጠ​ራ​ቸው፤ አራት መቶ ሺህ#ዕብ. “ሁለት መቶ ሺህ” ይላል እግ​ረ​ኞች፥ ከይ​ሁ​ዳም ሠላሳ ሺህ#ዕብ. “ዐሥር ሺህ” ይላል። ሰዎች ነበሩ። 5ሳኦ​ልም ወደ አማ​ሌቅ ከተማ ወጣ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ተደ​በቀ። 6ሳኦ​ልም ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና” አላ​ቸው። ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ወጡ። 7ሳኦ​ልም አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ከኤ​ው​ላጥ ጀምሮ በግ​ብፅ ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ሱር ድረስ መታ​ቸው። 8የአ​ማ​ሌ​ቅ​ንም ንጉሥ አጋ​ግን በሕ​ይ​ወቱ ማረ​ከው፤ የኢ​ያ​ሬ​ም​ንም ሕዝብ ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት ፈጽሞ አጠ​ፋ​ቸው። 9ነገር ግን ሳኦ​ልና ሕዝቡ ሁሉ አጋ​ግን፥ ከከ​ብ​ቱና ከበጉ መንጋ መል​ካም መል​ካ​ሙን፥ እህ​ሉ​ንም፥ ወይ​ኑ​ንም፥ መል​ካም የሆ​ነ​ውን ሁሉ አዳኑ። ፈጽ​መው ሊያ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ዱም፤ ነገር ግን የተ​ና​ቀ​ውን ሁሉ ፈጽ​መው አጠ​ፉት።
ሳኦል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተናቀ
10የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ሳሙ​ኤል መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፦ 11“ሳኦል እኔን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሶ​አ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም አል​ፈ​ጸ​መ​ምና ስላ​ነ​ገ​ሥ​ሁት ተጸ​ጸ​ትሁ።” ሳሙ​ኤ​ልም አዘነ። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ። 12ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ራ​ኤ​ልን ለመ​ገ​ና​ኘት በጥ​ዋት ገሥ​ግሦ ሄደ። ለሳ​ሙ​ኤ​ልም፥ “ሳኦል ወደ ቀር​ሜ​ሎስ መጣ፤ እነ​ሆም፥ ለራሱ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገ​ሩት። ሳሙ​ኤ​ልም ሰረ​ገ​ላ​ውን መልሶ ወደ ጌል​ጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአ​ማ​ሌቅ ዘንድ ከአ​መ​ጣ​ውም ከአ​ማ​ረው ከም​ር​ኮው መንጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሲሠዋ አገ​ኘው፤ 13ሳሙ​ኤ​ልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦ​ልም፥ “አንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረ​ክህ ሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ፈጽ​ሜ​አ​ለሁ” አለው። 14ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ይህ በጆ​ሮዬ የም​ሰ​ማው የበ​ጎች ጩኸ​ትና የበ​ሬ​ዎች ግሣት ምን​ድር ነው?” አለ። 15ሳኦ​ልም፦“ሕዝቡ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠ​ዉ​አ​ቸው ዘንድ ከበ​ጎ​ችና ከላ​ሞች መን​ጋ​ዎች መል​ካም መል​ካ​ሙን አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን አመ​ጣን፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ፈጽሜ አጠ​ፋሁ” አለው። 16ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ሌሊት የነ​ገ​ረ​ኝን ልን​ገ​ርህ” አለው፤ እር​ሱም፥ “ተና​ገር” አለው።
17ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን አለው፥ “በፊቱ ምንም ታናሽ ብት​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች አለቃ አል​ሆ​ን​ህ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ። 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሄደህ ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ቹን አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ፈጽ​መህ አጥ​ፋ​ቸው፤ እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ውጋ​ቸው ብሎ በመ​ን​ገድ ላከህ። 19ለም​ርኮ ሳስ​ተህ ለምን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህም? ለም​ንስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረ​ግህ?” 20ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሕ​ዝ​ቡን ቃል” ይላል። ስለ​ሰ​ማሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ከኝ መን​ገድ ሄጃ​ለሁ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን ንጉሥ አጋ​ግ​ንም አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ን​ንም ፈጽሜ አጥ​ፍ​ቻ​ለሁ። 21ሕዝቡ ግን ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጌ​ል​ጌላ ይሠዉ ዘንድ ከእ​ርሙ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ከም​ር​ኮው ወሰዱ” አለው። 22ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በመ​ስ​ማት ደስ እን​ደ​ሚ​ለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ቃ​ጠ​ልና በሚ​ታ​ረድ መሥ​ዋ​ዕት ደስ ይለ​ዋ​ልን? እነሆ፥ መታ​ዘዝ ከመ​ሥ​ዋ​ዕት፥ ማዳ​መ​ጥም የአ​ውራ በግ ስብ ከማ​ቅ​ረብ ይበ​ል​ጣል። 23ኀጢ​ኣት እንደ ምዋ​ር​ተ​ኝ​ነት ናትና አም​ል​ኮተ ጣዖ​ትም ደዌ​ንና ኀዘ​ንን ያመ​ጣል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ንቀ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ እን​ዳ​ት​ሆን ናቀህ” አለው።
24ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሕዝ​ቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላ​ቸ​ው​ንም ስለ ሰማሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዝና የአ​ን​ተን ቃል በመ​ተ​ላ​ለፍ በድ​ያ​ለሁ። 25አሁ​ንም እባ​ክህ ኀጢ​ኣ​ቴን ይቅር በለኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እሰ​ግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመ​ለስ” አለው። 26ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ንቀ​ሃ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዳ​ት​ሆን ንቆ​ሃ​ልና ከአ​ንተ ጋር አል​መ​ለ​ስም” አለው። 27ሳሙ​ኤ​ልም ሊሄድ ዘወር ባለ ጊዜ ሳኦል የል​ብ​ሱን ጫፍ ያዘ፤ ተቀ​ደ​ደም። 28ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል መን​ግ​ሥ​ት​ህን ዛሬ ከእ​ጅህ ቀደ​ዳት፤ ከአ​ን​ተም ለሚ​ሻል ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ 29እስ​ራ​ኤል ለሁ​ለት ይከ​ፈ​ላል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም አይ​ሰ​በ​ሰ​ብም፤#“እስ​ራ​ኤል ከሁ​ለት ይከ​ፈ​ላል” የሚ​ለው በዕብ. የለም “ከእ​ን​ግ​ዲህ አይ​ሰ​በ​ሰ​ብም” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ሰው የሚ​ጸ​ጸት አይ​ደ​ለ​ምና አይ​ጸ​ጸ​ትም” አለው። 30ሳኦ​ልም፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ አሁ​ንም በሕ​ዝቤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ፊትና በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እባ​ክህ አክ​ብ​ረኝ፤ ለአ​ም​ላ​ክ​ህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመ​ለስ” አለው። 31ሳሙ​ኤ​ልም ከሳ​ኦል በኋላ ተመ​ለሰ፤ ሳኦ​ልም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ።
32ሳሙ​ኤ​ልም፥ “የአ​ማ​ሌ​ቅን ንጉሥ አጋ​ግን አም​ጡ​ልኝ” አለ። አጋ​ግም እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ ወደ እርሱ መጣ። አጋ​ግም፥ “በውኑ ሞት እን​ደ​ዚህ መራራ ነውን?” አለ። 33ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን፥ “ሰይ​ፍህ ሴቶ​ችን ልጆች አልባ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ቻ​ቸው እን​ዲሁ እና​ትህ በሴ​ቶች መካ​ከል ልጅ አልባ ትሆ​ና​ለች” አለ፥ ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ ወጋው።
34ሳሙ​ኤ​ልም ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ፤ ሳኦ​ልም ወደ ቤቱ ወደ ገባ​ዖን ወጣ። 35ሳሙ​ኤ​ልም እስከ ሞተ​በት ቀን ድረስ ሳኦ​ልን ለማ​የት ዳግ​መኛ አል​ሄ​ደም፤ ሳሙ​ኤ​ልም ለሳ​ኦል አለ​ቀሰ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሳኦ​ልን ስላ​ነ​ገሠ ተጸ​ጸተ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ