የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 14

14
ዮና​ታን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ አደጋ እንደ ጣለ
1በነ​ጋም ጊዜ፥ የሳ​ኦል ልጅ ዮና​ታን ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “ና፤ በዚያ በኩል ወዳ​ለው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር እን​ለፍ” አለው፤ ለአ​ባ​ቱም አል​ነ​ገ​ረ​ውም። 2ሳኦ​ልም በመ​ጌ​ዶን ባለው በሮ​ማኑ ዛፍ በታች በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ረው ሕዝብ ስድ​ስት መቶ የሚ​ያ​ህል ሰው ነበረ። 3የዔሊ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የዮ​ካ​ብድ ወን​ድም፥ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ በሴሎ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህን የሆነ፥ ኤፉ​ድም የለ​በሰ አኪያ አብሮ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ዮና​ታን እንደ ሄደ አላ​ወ​ቁም ነበር። 4ዮና​ታ​ንም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ሊሻ​ገ​ር​በት በወ​ደ​ደው መተ​ላ​ለ​ፊያ መካ​ከል በወ​ዲህ አንድ ሾጣጣ፥ በወ​ዲ​ህም አንድ ሾጣጣ ድን​ጋ​ዮች ነበሩ፤ የአ​ን​ዱም ስም ባዚስ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሴና ነበረ። 5አን​ደ​ኛዋ መን​ገድ በማ​ኪ​ማስ አን​ጻር በመ​ስዕ በኩል የም​ት​መጣ ናት፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዋም መን​ገድ በገ​ባ​ዖን አን​ጻር በአ​ዜብ በኩል የም​ት​መጣ ነበ​ረች።
6ዮና​ታ​ንም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “ና፥ ወደ እነ​ዚህ ቈላ​ፋን ሰፈር እን​ለፍ፤ በብዙ ወይም በጥ​ቂት ማዳን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አያ​ስ​ቸ​ግ​ረ​ው​ምና ምና​ል​ባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳን ይሆ​ናል” አለው። 7ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም፥ “ልብህ ያሰ​ኘ​ህን ሁሉ አድ​ርግ እነሆ፥ ከአ​ንተ ጋር ነኝ፤ እንደ አንተ ልብ የእ​ኔም ልብ እን​ዲሁ ነው” አለው። 8ዮና​ታ​ንም አለው፥ “እነሆ፥ ወደ ሰዎቹ እና​ል​ፋ​ለን፤ ወደ እነ​ር​ሱም እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ 9እነ​ር​ሱም፦ እስ​ክ​ን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ድረስ ርቃ​ችሁ ቈዩ ቢሉን ርቀን እን​ቆ​ማ​ለን፤ ወደ እነ​ር​ሱም አን​ወ​ጣም። 10ነገር ግን ወደ እኛ ውጡ ቢሉን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና እን​ወ​ጣ​ለን፤ ምል​ክ​ታ​ች​ንም ይህ ይሆ​ናል።” 11ሁለ​ታ​ቸ​ውም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ገቡ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም “እነሆ፥ ዕብ​ራ​ው​ያን ከተ​ሸ​ሸ​ጉ​በት ጕድ​ጓድ ይወ​ጣሉ” አሉ። 12የሰ​ፈ​ሩም ሰዎች፦ ዮና​ታ​ን​ንና ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን “ወደ እኛ ውጡ፤ አንድ ነገ​ር​ንም እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን” አሉ። ዮና​ታ​ንም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ተከ​ተ​ለኝ” አለው። 13ዮና​ታ​ንም በእ​ጁና በእ​ግሩ ወጣ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ዮና​ታ​ንም ፊቱን መልሶ ገደ​ላ​ቸው፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም ተከ​ትሎ ገደ​ላ​ቸው። 14የዮ​ና​ታ​ንና የጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በወ​ን​ጭ​ፍና በዱላ የመ​ጀ​መ​ሪያ ግድ​ያ​ቸው በአ​ንድ ትልም እርሻ መካ​ከል ሃያ ያህል ሰው ነበረ። 15በሰ​ፈ​ሩና በእ​ር​ሻ​ውም ድን​ጋጤ ሆነ፤ በሰ​ፈሩ የተ​ቀ​መጡ ሕዝ​ብና የሚ​ዋ​ጉ​ትም ሁሉ ተሸ​በሩ፤ መዋ​ጋ​ትም አል​ቻ​ሉም፤ ምድ​ሪ​ቱም ተና​ወ​ጠች፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ታላቅ ድን​ጋጤ መጣ።
የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ድል መሆን
16በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ያሉ የሳ​ኦል ዘበ​ኞ​ችም ተመ​ለ​ከቱ፤ እነ​ሆም፥ ሠራ​ዊቱ ወዲ​ህና ወዲያ እየ​ተ​ራ​ወጡ ተበ​ታ​ተኑ። 17ሳኦ​ልም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ “እስኪ ተቋ​ጠሩ፤ ከእኛ ዘንድ የሄደ ማን እንደ ሆነ ተመ​ል​ከቱ” አላ​ቸው። በተ​ቋ​ጠ​ሩም ጊዜ እነሆ፥ ዮና​ታ​ንና ጋሻ ጃግ​ሬው በዚያ አል​ተ​ገ​ኙም። 18በዚ​ያም ቀን አኪያ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ኤፉድ ይለ​ብስ ነበ​ርና ሳኦል፥ “ኤፉ​ድን አምጣ” አለው። 19ሳኦ​ልም ከካ​ህኑ ጋር ሲነ​ጋ​ገር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መን​ደር ግር​ግ​ርታ እየ​በዛ ሄደ፤ ሳኦ​ልም ካህ​ኑን፥ “እጅ​ህን መልስ” አለው። 20ሳኦ​ልና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ውጊ​ያው መጡ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ሰይፍ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ነበረ፤ እጅ​ግም ታላቅ ሽብር ሆነ። 21ቀድሞ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር የነ​በ​ሩና ወደ ሠራ​ዊቱ የወጡ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሳ​ኦ​ልና ከዮ​ና​ታን ጋር ወደ ነበሩ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ለመ​ሆን ተመ​ለሱ። 22በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር የተ​ሸ​ሸ​ጉት እስ​ራ​ኤል ሁሉ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እንደ ሸሹ በሰሙ ጊዜ እነ​ርሱ ደግሞ ሊዋ​ጉ​አ​ቸው ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው። 23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን እስ​ራ​ኤ​ልን አዳነ፤ ውጊ​ያ​ውም በባ​ሞት በኩል አለፈ። ከሳ​ኦ​ልም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ዐሥር ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ውጊ​ያ​ውም በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ሬም ከተማ ሁሉ ተበ​ታ​ትኖ ነበር።
ከጦ​ር​ነት በኋላ የተ​ፈ​ጸሙ ድር​ጊ​ቶች
24ሳኦ​ልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላ​ቶቼን እስ​ክ​በ​ቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና። ሕዝ​ቡም ሁሉ እህል አል​ቀ​መ​ሱም። ሀገ​ሩም ሁሉ ምሳ አል​በ​ላም። 25ብዙ ንብ ያለ​በት የማር ቀፎም በዱሩ ይታይ ነበር። 26ሕዝ​ቡም ማር ወደ አለ​በት ቀፎ ሄዱ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይነ​ጋ​ገሩ ነበር። እነ​ሆም፥ ሕዝቡ መሐ​ላ​ውን ፈርቶ ነበ​ርና ማንም እጁን አን​ሥቶ ወደ አፉ አላ​ደ​ረ​ገም። 27ዮና​ታን ግን አባቱ ሕዝ​ቡን ባማለ ጊዜ አል​ሰ​ማም ነበር፤ እር​ሱም በእጁ ያለ​ች​ውን በትር አን​ሥቶ ጫፍ​ዋን ወደ ወለ​ላው ነከረ፤ እጁ​ንም ወደ አፉ አደ​ረገ፤ ዐይ​ኑም በራ። 28ከሕ​ዝ​ቡም አንድ ሰው መልሶ፥ “አባ​ትህ፦ ዛሬ መብል የሚ​በላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝ​ቡን መሐላ አም​ሎ​አ​ቸ​ዋል” አለው፤ ሕዝ​ቡም ደከሙ። 29ዮና​ታ​ንም “አባቴ ምድ​ሪ​ቱን አስ​ቸ​ገረ፤ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀ​ምስ ዐይኔ እንደ በራ እዩ፤ 30ይል​ቅስ ሕዝቡ ካገ​ኙት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምርኮ በል​ተው ቢሆን ኑሮ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መመ​ታት ይበ​ልጥ አል​ነ​በ​ረ​ምን?” አለ።
31በዚ​ያም ቀን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በማ​ኪ​ማስ#ዕብ. “ከማ​ኪ​ማስ እስከ ኤሎን” የሚል ይጨ​ም​ራል። መቱ​አ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም እጅግ ደከሙ። 32ሕዝ​ቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎ​ችን፥ በሬ​ዎ​ች​ንም፥ ጥጆ​ች​ንም ወስ​ደው እን​ዳ​ገኙ በም​ድር ላይ አረዱ፤ ሕዝ​ቡም ከደሙ ጋር በሉ። 33ለሳ​ኦ​ልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመ​ብ​ላ​ታ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደሉ” ብለው ነገ​ሩት። ሳኦ​ልም በጌ​ቴም “ትልቅ ድን​ጋይ አን​ከ​ባ​ል​ላ​ችሁ አቅ​ር​ቡ​ልኝ” አላ​ቸው። 34ሳኦ​ልም፥ “በሕ​ዝቡ መካ​ከል እየ​ዞ​ራ​ችሁ፦ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው በሬ​ው​ንና በጉን ወደ እኔ ያቅ​ርብ፥ በዚ​ህም እረ​ዱና ብሉ፤ ከደ​ሙም ጋር በመ​ብ​ላ​ታ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​በ​ድሉ” በሉ​አ​ቸው አለ። እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሰው ሁሉ በእጁ ያለ​ውን በዚ​ያች ሌሊት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም አረ​ደው። 35ሳኦ​ልም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ ይኸ​ውም ሳኦል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሠ​ራው የመ​ጀ​መ​ሪያ መሠ​ዊያ ነው።
36ሳኦ​ልም፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በሌ​ሊት ተከ​ት​ለን እን​ው​ረድ፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ እን​በ​ዝ​ብ​ዛ​ቸው፤ አንድ ሰው እንኳ አና​ስ​ቀ​ር​ላ​ቸው” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ” አሉት። ካህ​ኑም፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ቅ​ረብ” አለ። 37ሳኦ​ልም፥ “ልው​ረ​ድና ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ልከ​ተ​ልን? በእ​ስ​ራ​ኤ​ልስ እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ህን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየ​ቀው። በዚያ ቀን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም። 38ሳኦ​ልም፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ችን ሁሉ ወደ​ዚህ አቅ​ርቡ፤ ዛሬ ይህ ኀጢ​ኣት በማን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ 39እስ​ራ​ኤ​ልን የሚ​ያ​ድን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ኀጢ​ኣቱ በልጄ በዮ​ና​ታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለ። ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ አንድ የመ​ለ​ሰ​ለት ሰው አል​ነ​በ​ረም። 40እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ፥ “እና​ንተ አንድ ወገን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔና ልጄ ዮና​ታ​ንም አንድ ወገን እን​ሆ​ና​ለን” አለ። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ርግ” አሉት። 41ሳኦ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ዛሬ ያል​መ​ለ​ስ​ህ​ልኝ ስለ ምን​ድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮ​ና​ታ​ንም እንደ ሆነች አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተና​ገር። ዕጣው ይህን የሚ​ገ​ልጥ ከሆነ ለሕ​ዝ​ብህ ለእ​ስ​ራ​ኤል እው​ነ​ትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮ​ና​ታ​ንና በሳ​ኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝ​ቡም ነፃ ወጣ። 42ሳኦ​ልም፥ “በእ​ኔና በዮ​ና​ታን መካ​ከል ዕጣ አጣ​ጥ​ሉን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕጣ ያወ​ጣ​በ​ትም ይሞ​ታል” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “እን​ዲህ ያለ ነገር አይ​ሆ​ንም” አሉት፤ ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን እንቢ አላ​ቸው። በእ​ር​ሱና በልጁ በዮ​ና​ታን መካ​ከ​ልም ዕጣ አጣ​ጣሉ። ዕጣ​ውም በልጁ በዮ​ና​ታን ላይ ወጣ።
43ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ንገ​ረኝ” አለው፤ ዮና​ታ​ንም፥ “በእጄ ባለው በበ​ትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በር​ግጥ ቀም​ሻ​ለሁ፤ እነ​ሆኝ፥ እሞ​ታ​ለሁ” ብሎ ነገ​ረው። 44ሳኦ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ግ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይጨ​ም​ር​ብኝ፤ ዛሬ ፈጽ​መህ ትሞ​ታ​ለህ” አለ። 45ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት ያደ​ረገ ዮና​ታን ዛሬ ይሞ​ታ​ልን? ይህ አይ​ሁን፤ ዛሬ ለሕ​ዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከራሱ ጠጕር አን​ዲት በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም” አሉት። ሕዝ​ቡም ያን ጊዜ ስለ ዮና​ታን ጸለዩ፤ እር​ሱም አል​ተ​ገ​ደ​ለም። 46ሳኦ​ልም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ከመ​ከ​ተል ተመ​ለሰ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ስፍ​ራ​ቸው ሄዱ።
የሳ​ኦል ዘመነ መን​ግ​ሥ​ትና ቤተ ሰቡ
47ሳኦ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አጸና፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉት ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞ​ዓ​ብም፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ ከቢ​ዖ​ርም፥ ከሱ​ባም ነገ​ሥ​ታት፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየ​ሄ​ደ​በ​ትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር። 48እር​ሱም ጀግና ነበረ፤ አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ን​ንም መታ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ከዘ​ራ​ፊ​ዎቹ እጅ አዳነ።
49የሳ​ኦ​ልም ወን​ዶች ልጆች ዮና​ታን፥ የሱዊ፥ ሚል​ኪሳ ነበሩ፤ የሁ​ለ​ቱም ሴቶች ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ሜሮብ፥ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ሜል​ኮል ነበረ። 50የሳ​ኦ​ልም ሚስት ስም የአ​ኪ​ማ​ኦስ ልጅ አኪ​ና​ሆም ነበ​ረች፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ስም የሳ​ኦል አጎት የኔር ልጅ አቤ​ኔር ነበረ። 51የሳ​ኦ​ልም አባት ቂስ ነበረ፤ የአ​ቤ​ኔ​ርም አባት የአ​ብ​ኤል ልጅ የያ​ሚን ልጅ ኔር ነበረ።
52በሳ​ኦ​ልም ዘመን ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጽኑ ውጊያ ነበረ፤ ሳኦ​ልም ጽኑ ወይም ኀያል ሰው ባየ ጊዜ ወደ እርሱ ይሰ​በ​ስብ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ