የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 10

10
ሳሙ​ኤል ሳኦ​ልን ቀብቶ እንደ አነ​ገ​ሠው
1ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው። 2ዛሬ ከእኔ በተ​ለ​የህ ጊዜ በብ​ን​ያም ግዛት በቤ​ቴል አው​ራጃ በራ​ሔል መቃ​ብር አጠ​ገብ ሁለት ሰዎች እየ​ቸ​ኰሉ ሲሄዱ ታገ​ኛ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም፦ ልት​ፈ​ል​ጉ​አ​ቸው ሂዳ​ችሁ የነ​በ​ራ​ች​ሁ​ላ​ቸው አህ​ዮች ተገ​ኝ​ተ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ አባ​ትህ ስለ አህ​ዮቹ ማሰብ ትቶ፦ የል​ጄን ነገር እን​ዴት አደ​ር​ጋ​ለሁ? እያለ ስለ እና​ንተ ይጨ​ነ​ቃል ይሉ​ሃል። 3ከዚ​ያም ደግሞ አል​ፈህ፥ ወደ ትልቁ የታ​ቦር ዛፍ ትደ​ር​ሳ​ለህ፤ በዚ​ያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍ​የል ጠቦ​ቶች ሲነዳ፥ ሁለ​ተ​ኛው ሦስት የዳቦ ስልቻ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ ይዘው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ታገ​ኛ​ለህ፤ 4ሰላ​ም​ታም ይሰ​ጡ​ሃል፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ሁለት ዳቦ​ዎ​ችም ይሰ​ጡ​ሃል፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም ትቀ​በ​ላ​ለህ። 5ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ። 6የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በአ​ንተ ይወ​ር​ዳል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ትን​ቢት ትና​ገ​ራ​ለህ፤ እንደ ሌላም ሰው ሆነህ ትለ​ወ​ጣ​ለህ። 7እነ​ዚ​ህም ምል​ክ​ቶች በደ​ረ​ሱህ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና እጅህ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ አድ​ርግ። 8በፊ​ቴም ወደ ጌል​ገላ ትወ​ር​ዳ​ለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ርብ ዘንድ፥ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስ​ክ​መ​ጣና የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን እስ​ከ​ም​ነ​ግ​ርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈ​ያ​ለህ።”
9ከሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘንድ ለመ​ሄድ ፊቱን በመ​ለሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሌላ ልብ ለወ​ጠ​ለት፤ በዚ​ያም ቀን እነ​ዚህ ምል​ክ​ቶች ሁሉ ደረ​ሱ​ለት። 10ወደ​ዚ​ያም ኮረ​ብታ በደ​ረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነ​ቢ​ያት ጉባኤ አገ​ኙት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ወረደ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ። 11ቀድ​ሞም የሚ​ያ​ው​ቁት ሁሉ በነ​ቢ​ያት መካ​ከል ባዩት ጊዜ ሕዝቡ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “በቂስ ልጅ ላይ የሆ​ነው ምን​ድን ነው? በውኑ ሳኦል ከነ​ቢ​ያት ወገን ነውን?” ተባ​ባሉ። 12ከዚ​ያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፥ “አባ​ቱስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለ​ዚ​ህም “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌ ሆነ። 13ትን​ቢት መና​ገ​ሩ​ንም በፈ​ጸመ ጊዜ ወደ ኮረ​ብ​ታው ወጣ።
14ከቤተ ሰቡም አንዱ እር​ሱ​ንና ብላ​ቴ​ና​ውን፥ “ወዴት ሄዳ​ችሁ ኖሮ​አል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አህ​ዮ​ችን ልን​ፈ​ልግ ሄደን ነበር፤ ባጣ​ና​ቸ​ውም ጊዜ ወደ ሳሙ​ኤል መጣን” አሉት። 15ያም ቤተ ሰብ፥ “ሳሙ​ኤል ምን አለ? እባ​ክህ! ንገ​ረኝ” አለው፤ 16ሳኦ​ልም ለቤተ ሰቡ፥ “አህ​ዮች እንደ ተገኙ ገለ​ጠ​ልን” አለው፤ ነገር ግን የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ነገር አላ​ወ​ራ​ለ​ትም።
የሳ​ኦል ንጉሥ መሆን በይፋ እንደ ተነ​ገረ
17ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ እን​ዲ​ሄዱ አዘ​ዛ​ቸው። 18የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ አወ​ጣሁ፤ ከግ​ብፅ ንጉሥ ከፈ​ር​ዖ​ንም እጅ፥ ከሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ሁም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እጅ አዳ​ን​ኋ​ችሁ’ አላ​ቸው። 19ዛሬ ግን ከመ​ከ​ራ​ች​ሁና ከጭ​ን​ቃ​ችሁ ሁሉ ያዳ​ና​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ችሁ፦ ‘እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን’ አላ​ች​ሁት። አሁ​ንም በየ​ነ​ገ​ዳ​ች​ሁና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁሙ” አላ​ቸው። 20ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ዶች ሁሉ አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በብ​ን​ያም ወገን ላይ ወደቀ። 21የብ​ን​ያ​ም​ንም ነገድ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በማ​ጥር ወገን ላይ ወደቀ፤ የማ​ጥ​ር​ንም ወገን በየ​ሰዉ አቀ​ረበ፤ ዕጣ​ውም በቂስ ልጅ በሳ​ኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለ​ገ​ውም፤ አላ​ገ​ኘ​ው​ምም። 22ሳሙ​ኤ​ልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካ​ከል ተሸ​ሽ​ጎ​አል” ብሎ መለሰ። 23እር​ሱም ሮጦ ከዚያ አመ​ጣው፤ እር​ሱም በሕ​ዝቡ መካ​ከል አቆ​መው፤ ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ይልቅ ረዥም ነበረ፤ ሕዝ​ቡም ከት​ከ​ሻው በታች ሆኑ። 24ሳሙ​ኤ​ልም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “ከሕ​ዝቡ ሁሉ እር​ሱን የሚ​መ​ስል እንደ ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጠ​ውን ታያ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ንጉሥ ሕያው ይሁን” እያሉ እል​ልታ አደ​ረጉ።
25ሳሙ​ኤ​ልም የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ነገ​ራ​ቸው፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው አሰ​ና​በ​ታ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ። 26ሳኦ​ልም ወደ ቤቱ ወደ ገባ​ዖን ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን የነ​ካው ኀያ​ላ​ንም ከሳ​ኦል ጋር ሄዱ። 27ክፉ​ዎች ሰዎች ግን፥ “ያድ​ነን ዘንድ ይህ ሰው ማን ነው?” ብለው ናቁት፤ እጅ መን​ሻም አላ​መ​ጡ​ለ​ትም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ