የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 22

22
ነቢዩ ሚክ​ያስ ንጉሥ አክ​ዓ​ብን እን​ዳ​ስ​ጠ​ነ​ቀ​ቀው
(2ዜ.መ. 18፥2-27)
1በሰ​ማ​ር​ያም ሦስት ዓመት ተቀ​መጠ፤ በሶ​ር​ያና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል ጦር​ነት አል​ነ​በ​ረም። 2ከዚ​ህም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወረደ። 3የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ የእኛ እንደ ሆነች፥ እኛም ከሶ​ርያ ንጉሥ እጅ ሳን​ወ​ስ​ዳት ዝም እን​ዳ​ልን ታው​ቃ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። 4የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ እን​ዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትዘ​ም​ታ​ለ​ህን?” አለው። ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ለእ​ስ​ራ​እል ንጉሥ፥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለው።
5የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ጠይ​ቁ​ልን” አለው። 6የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ነቢ​ያ​ቱን አራት መቶ የሚ​ያ​ህ​ሉ​ትን ሰዎች ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ውጣ” አሉት። 7ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እን​ጠ​ይ​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ በዚህ አይ​ገ​ኝ​ምን?” አለው። 8የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ን​ጠ​ይ​ቅ​በት የይ​ምላ ልጅ ሚክ​ያስ የሚ​ባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መል​ካም አይ​ና​ገ​ር​ል​ኝ​ምና እጠ​ላ​ዋ​ለሁ” አለው። የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “ንጉሥ እን​ዲህ አይ​በል” አለ። 9የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አን​ዱን ጃን​ደ​ረባ ጠርቶ፥ “የይ​ም​ላን ልጅ ሚክ​ያ​ስን ፈጥ​ነህ ጥራው” አለው። 10የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አክ​ዓ​ብና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸው ጋር በሰ​ማ​ርያ በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ በአ​ደ​ባ​ባይ በዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ነቢ​ያ​ቱም ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ትን​ቢት ተና​ገሩ። 11የከ​ሓና ልጅ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም የብ​ረት ቀን​ዶች ሠርቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በእ​ነ​ዚህ ቀን​ዶች ሶር​ያ​ው​ያ​ንን ትወ​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ” አለ። 12ነቢ​ያ​ትም ሁሉ እን​ዲህ ብለው ትን​ቢት ተና​ገሩ፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ዝመት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይረ​ዳ​ሃል። ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።”
13ሚክ​ያ​ስ​ንም ሊጠራ የሄደ መል​እ​ክ​ተኛ፥ “እነሆ፥ ነቢ​ያት ሁሉ በአ​ንድ አፍ ሆነው ለን​ጉሡ መል​ካ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል​ህም እንደ ቃላ​ቸው እን​ዲ​ሆን መል​ካም እን​ድ​ት​ና​ገር እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው። 14ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ። 15ወደ ንጉ​ሡም ደረሰ። ንጉ​ሡም፥ “ሚክ​ያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ እን​ሂ​ድን? ወይስ እን​ቅር?” አለው። እር​ሱም፥ “ውጣና ተከ​ና​ወን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በን​ጉሡ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታል” ብሎ መለ​ሰ​ለት። 16ንጉ​ሡም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እው​ነት ትነ​ግ​ረኝ ዘንድ ስንት ጊዜ አም​ል​ሃ​ለሁ?” አለው። 17እር​ሱም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ጠባቂ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው በጎች በተ​ራ​ሮች ላይ ተበ​ት​ነው አየሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ነ​ዚህ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ምን? እያ​ን​ዳ​ንዱ በሰ​ላም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ።” 18የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥን፥ “ክፉ እንጂ መል​ካም እን​ደ​ማ​ይ​ና​ገ​ር​ልኝ አላ​ል​ሁ​ምን?” አለው። 19ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሰ​ማ​ሁት እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው ቆመው አየሁ። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ወጥቶ በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ይወ​ድቅ ዘንድ አክ​ዓ​ብን የሚ​ያ​ሳ​ስት ማን ነው? አለ። አን​ዱም እን​ዲህ ያለ ነገር፥ ሌላ​ውም እን​ዲያ ያለ ነገር ተና​ገረ። 21መን​ፈ​ስም ወጣ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አስ​ተ​ዋ​ለሁ አለ። 22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ በምን ታስ​ተ​ዋ​ለህ? አለው፤ እር​ሱም ወጥቼ በነ​ቢ​ያቱ ሁሉ አፍ ሐሰ​ተኛ መን​ፈስ እሆ​ና​ለሁ አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ማሳ​ሳ​ትስ ታሳ​ስ​ተ​ዋ​ለህ፤ ይሆ​ን​ል​ሃ​ልም፤ ውጣ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርግ አለ። 23አሁ​ንም፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በነ​ቢ​ያ​ትህ ሁሉ አፍ ሐሰ​ተኛ መን​ፈስ አድ​ር​ጎ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በላ​ይህ ክፉ ተና​ግ​ሮ​ብ​ሃል።”
24የከ​ሓ​ናም ልጅ ሴዴ​ቅ​ያስ ቀረበ፤ ሚክ​ያ​ስ​ንም ጕን​ጩን በጥፊ መታ​ውና፥ “ምን ዓይ​ነት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነው የተ​ና​ገ​ረህ?” አለው። 25ሚክ​ያ​ስም፥ “እነሆ፥ በዚያ ቀን ልት​ሸ​ሸግ ወደ ውስ​ጠ​ኛው እል​ፍ​ኝህ በሄ​ድህ ጊዜ ታያ​ለህ” አለ። 26የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “ሚክ​ያ​ስን ውሰዱ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ሹም ወደ አሞን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኤሚር” ይላል። ወደ ንጉ​ሡም ልጅ ወደ ኢዮ​አስ መል​ሳ​ችሁ፦ 27ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ በደ​ኅና እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ይህን ሰው በግ​ዞት አኑ​ሩት፤ የመ​ከ​ራም እን​ጀራ መግ​ቡት፤ የመ​ከ​ራም ውኃ አጠ​ጡት በሉ​አ​ቸው” አለ። 28ሚክ​ያ​ስም፥ “በሰ​ላም ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለም” አለ። ደግ​ሞም አሕ​ዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ” አለ።#“ደግ​ሞም አሕ​ዛብ ሁሉ ሆይ ስሙኝ አለ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
የን​ጉሥ አክ​ዓብ ሞት
(2ዜ.መ. 18፥28-34)
29የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ዘመቱ። 30የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ልብ​ሴን ለውጬ ወደ ሰልፍ እገ​ባ​ለሁ፤ አንተ ግን የእ​ኔን ልብስ ልበስ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ልብ​ሱን ለውጦ ወደ ሰልፍ ገባ። 31የሶ​ር​ያም ንጉሥ ሠላሳ ሁለ​ቱን የሰ​ረ​ገ​ሎች አለ​ቆች፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በቀር፥ ታናሽ ቢሆን ወይም ታላቅ ከማ​ና​ቸ​ውም ጋር አትዋጉ” ብሎ አዝዞ ነበር። 32የሰ​ረ​ገ​ሎች አለ​ቆ​ችም የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “በእ​ው​ነት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ይመ​ስ​ላል፤” አሉ ይዋ​ጉ​ትም ዘንድ ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ጮኸ። 33የሰ​ረ​ገ​ሎች አለ​ቆ​ችም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እን​ዳ​ል​ሆነ ባዩ ጊዜ እር​ሱን ከማ​ሳ​ደድ ተመ​ለሱ። 34አንድ ሰውም ቀስ​ቱን ድን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በሳ​ን​ባ​ውና በደ​ረቱ መካ​ከል ወጋው፤ ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “መል​ሰህ ንዳ፤ ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና ከሰ​ልፍ ውስጥ አው​ጣኝ” አለው። 35በዚ​ያም ቀን ሰልፍ በረታ፤ ንጉ​ሡም ከጥ​ዋት እስከ ማታ በሶ​ር​ያ​ው​ያን ፊት በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተደ​ግፎ ነበር፤ የቍ​ስ​ሉም ደም በሰ​ረ​ገ​ላው ውስጥ ፈሰሰ፤ ማታም ሞተ። 36ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ አዋጅ ነጋ​ሪው ወጥቶ፥ “ንጉሡ ሞቶ​አ​ልና እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ከተ​ማው፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ሀገሩ ይሂድ” ብሎ አዋጅ ነገረ።
37ወደ ሰማ​ር​ያም መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም በሰ​ማ​ርያ ቀበ​ሩት፤ 38ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም በሰ​ማ​ርያ ምንጭ አጠ​ቡት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በነ​ቢዩ አድሮ እንደ ተና​ገረ ውሾ​ችና ጅቦች ደሙን ላሱት። አመ​ን​ዝ​ሮች ሴቶ​ችም በደሙ ታጠ​ቡ​በት። 39የቀ​ረ​ውም የአ​ክ​ዓብ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ነገር ሁሉ፥ ከዝ​ሆን ጥር​ስም የሠ​ራው ቤት፥ የሠ​ራ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ሁሉ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። 40አክ​ዓ​ብም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።
ስለ ይሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሳ​ፍጥ
(2ዜ.መ. 20፥31—21፥1)
41የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ አክ​ዓ​ብም በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት የአሳ ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ በይ​ሁዳ ላይ ነገሠ። 42ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ አም​ስት ዓመት ጎበዝ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ አም​ስት ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ዓዙባ የተ​ባ​ለች የሴ​ሜይ ልጅ ነበ​ረች። 43በአ​ባ​ቱም በአሳ መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ፈቀቅ አላ​ለም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን አደ​ረገ፤ ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን አላ​ራ​ቀም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር። 44ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ጋር ታረቀ።
45የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገር፥ ኀይ​ሉም፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። 46ከአ​ባ​ቱም ከአሳ ዘመን የቀ​ረ​ውን ርኩስ ሥራ ከም​ድር አጠፋ። 47በኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሹሙም እንደ ንጉሥ ነበረ። 48ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከ​ብን ሠራ፤ ነገር ግን መር​ከ​ቢቱ በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም። 49የአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮቼ ጋር በመ​ር​ከብ ይሂዱ” አለው፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን አል​ወ​ደ​ደም። 50ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።#ምዕ. 22 ከቍ. 47 እስከ 50 ያለው በግ​ሪኩ የለም።
51በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ በዐ​ሥራ ሰባ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ክ​ዓብ ልጅ አካ​ዝ​ያስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ሁለት ዓመት ነገሠ። 52በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ በአ​ባቱ በአ​ክ​ዓብ፥ በእ​ና​ቱም በኤ​ል​ዛ​ቤል መን​ገድ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባሳ​ተው በና​ባጥ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ ሄደ። 53በዓ​ሊ​ም​ንም አመ​ለከ፤ ሰገ​ደ​ላ​ቸ​ውም፤ ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ አባ​ቶቹ እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​ቈ​ጣው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ