መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 19:1-4

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 19:1-4 አማ2000

አክ​ዓ​ብም ኤል​ያስ ያደ​ረ​ገ​ውን፥ የሐ​ሰት ነቢ​ያ​ት​ንም ሁሉ በሰ​ይፍ እንደ ገደ​ላ​ቸው ለሚ​ስቱ ለኤ​ል​ዛ​ቤል ነገ​ራት። ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “አንተ ኤል​ያስ ከሆ​ንህ እኔም ኤል​ዛ​ቤል ከሆ​ንሁ ነገ በዚህ ጊዜ ሰው​ነ​ት​ህን ከእ​ነ​ዚህ እንደ አንዱ ሰው​ነት ባላ​ደ​ር​ጋት፥ አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ” ብላ ወደ ኤል​ያስ ላከች። ኤል​ያ​ስም ፈርቶ ተነሣ፤ ነፍ​ሱ​ንም ሊያ​ድን ሄደ፤ በይ​ሁ​ዳም ወዳ​ለው ወደ ቤር​ሳ​ቤህ መጥቶ ብላ​ቴ​ና​ውን በዚያ ተወ። እር​ሱም አንድ ቀን የሚ​ያ​ህል መን​ገድ በም​ድረ በዳ ሄደ፤ መጥ​ቶም ከደ​ድሆ ዛፍ በታች ተቀ​መ​ጠና፦ ይበ​ቃ​ኛል፤ አሁ​ንም አቤቱ! እኔ ከአ​ባ​ቶቼ አል​በ​ል​ጥ​ምና ነፍ​ሴን ውሰድ” ብሎ እን​ዲ​ሞት ለመነ።