መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 18:36-38

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 18:36-38 አማ2000

ነቢዩ ኤል​ያ​ስም ወደ ሰማይ አቅ​ንቶ ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ሆይ፥ ስማኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ ዛሬ በእ​ሳት ስማኝ፤ አንተ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አም​ላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪ​ያህ እንደ ሆንሁ፤ ይህ​ንም ሥራ ስለ አንተ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች ይወቁ። አንተ፥ አቤቱ፥ አም​ላክ እንደ ሆንህ፥ ልባ​ቸ​ው​ንም ደግሞ እንደ መለ​ስህ፤ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ ስማኝ፤ አቤቱ፥ ስማኝ” አለ። እሳ​ትም ከሰ​ማይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወረ​ደች፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ እን​ጨ​ቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በላች፤ በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ያለ​ውን ውኃ፥ አፈ​ሩ​ንም ላሰች።