መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 18:22-24

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 18:22-24 አማ2000

ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት አንድ እኔ ብቻ ቀር​ቻ​ለሁ፤ የበ​ዓል ነቢ​ያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ነቢ​ያ​ትም አራት መቶ ናቸው። ሁለት ወይ​ፈ​ኖች ይሰ​ጡን፤ እነ​ር​ሱም አንድ ወይ​ፈን ይም​ረጡ፤ እየ​ብ​ል​ቱም ይቍ​ረ​ጡት፤ በእ​ን​ጨ​ትም ላይ ያኑ​ሩት፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አይ​ጨ​ምሩ፤ እኔም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ወይ​ፈን አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ፤ በእ​ን​ጨ​ቱም ላይ አኖ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አል​ጨ​ም​ርም። እና​ን​ተም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈ​ጣ​ሪ​ዬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለሁ፤ ሰም​ቶም በእ​ሳት የሚ​መ​ልስ አም​ላክ፥ እርሱ አም​ላክ ይሁን።” ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መል​ካም ነው” ብለው መለሱ።