መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 18:17-39

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 18:17-39 አማ2000

አክ​ዓ​ብም ኤል​ያ​ስን ባየው ጊዜ፥ አክ​ዓብ ኤል​ያ​ስን፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ት​ገ​ለ​ባ​ብጥ አንተ ነህን?” አለው። ኤል​ያ​ስም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትታ​ችሁ በዓ​ሊ​ምን የተ​ከ​ተ​ላ​ችሁ፥ አን​ተና የአ​ባ​ትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔስ እስ​ራ​ኤ​ልን አል​ገ​ለ​ባ​ብ​ጥም። አሁ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ልከህ፥ አራት መቶ ሃምሳ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትን፥ አራት መቶ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ነቢ​ያ​ትን ወደ እኔ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሰብ​ስብ” አለው። አክ​ዓ​ብም ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ልኮ ነቢ​ያ​ቱን ሁሉ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው። ኤል​ያ​ስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁ​ለት አሳብ ታነ​ክ​ሳ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ፤ በዓ​ልም አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ” አለ። ሕዝ​ቡም አን​ዲት ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም። ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት አንድ እኔ ብቻ ቀር​ቻ​ለሁ፤ የበ​ዓል ነቢ​ያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ነቢ​ያ​ትም አራት መቶ ናቸው። ሁለት ወይ​ፈ​ኖች ይሰ​ጡን፤ እነ​ር​ሱም አንድ ወይ​ፈን ይም​ረጡ፤ እየ​ብ​ል​ቱም ይቍ​ረ​ጡት፤ በእ​ን​ጨ​ትም ላይ ያኑ​ሩት፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አይ​ጨ​ምሩ፤ እኔም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ወይ​ፈን አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ፤ በእ​ን​ጨ​ቱም ላይ አኖ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አል​ጨ​ም​ርም። እና​ን​ተም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈ​ጣ​ሪ​ዬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለሁ፤ ሰም​ቶም በእ​ሳት የሚ​መ​ልስ አም​ላክ፥ እርሱ አም​ላክ ይሁን።” ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መል​ካም ነው” ብለው መለሱ። ኤል​ያ​ስም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት፥ “እና​ንተ ብዙ​ዎች ናች​ሁና አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ አንድ ወይ​ፈን ምረ​ጡና አዘ​ጋጁ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም ስም ጥሩ፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አት​ጨ​ምሩ” አላ​ቸው። የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ወይ​ፈ​ንም ወስ​ደው አዘ​ጋጁ፤ ከጥ​ዋ​ትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበ​ዓ​ልን ስም ጠሩ። ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ የሠ​ሩ​ት​ንም መሠ​ዊያ እያ​ነ​ከሱ ይዞሩ ነበር። በቀ​ት​ርም ጊዜ ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ፥ “አም​ላክ ነውና በታ​ላቅ ቃል ጩኹ፤ ምና​ል​ባት ይጫ​ወት ይሆ​ናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆ​ናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀ​ስ​ቀስ ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል” እያለ ይዘ​ባ​በ​ት​ባ​ቸው ጀመር። በታ​ላ​ቅም ቃል ይጮኹ ጀመር፤ እንደ ልማ​ዳ​ቸ​ውም ደማ​ቸው እስ​ኪ​ፈ​ስስ ድረስ ገላ​ቸ​ውን በጦ​ርና በሰ​ይፍ ይብ​ዋ​ጭሩ ነበር። እስከ ሠር​ክም ድረስ ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር፤ ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስና የሚ​ያ​ደ​ም​ጥም አል​ነ​በ​ረም። ከዚ​ህም በኋላ መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ግ​በት ጊዜ ኤል​ያስ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትን፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲያ በቃ​ችሁ፤ ወግዱ፤ ሂዱም፥ እኔም መሥ​ዋ​ዕ​ቴን እሠ​ዋ​ለሁ” አላ​ቸው። ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ። ኤል​ያ​ስም፦ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይሆ​ናል የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ደረ​ሰ​ለት እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን ወሰደ። ድን​ጋ​ዮ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም መሠ​ዊያ አድ​ርጎ ሠራ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም መሠ​ዊያ አደሰ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ዙሪያ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ እህል የሚ​ይዝ ጕድ​ጓድ ቈፈረ። በሠ​ራ​ውም መሠ​ዊያ ላይ እን​ጨ​ቱን ደረ​ደረ፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በብ​ልት በብ​ልቱ ቈረጠ፤ በእ​ን​ጨ​ቱም ላይ አኖረ፤ “አራት ጋን ውኃ አም​ጡ​ልኝ፤ በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና በእ​ን​ጨቱ ላይም አፍ​ስሱ” አለ፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረጉ። ደግ​ሞም፥ “ድገሙ” አለ፤ እነ​ር​ሱም ደገሙ። እር​ሱም፥ “ሦስ​ተኛ አድ​ርጉ” አለ፤ ሦስ​ተ​ኛም አደ​ረጉ። ውኃ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ፈሰሰ። ደግ​ሞም ጕድ​ጓ​ዱን በውኃ ሞላው። ነቢዩ ኤል​ያ​ስም ወደ ሰማይ አቅ​ንቶ ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ሆይ፥ ስማኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ ዛሬ በእ​ሳት ስማኝ፤ አንተ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አም​ላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪ​ያህ እንደ ሆንሁ፤ ይህ​ንም ሥራ ስለ አንተ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች ይወቁ። አንተ፥ አቤቱ፥ አም​ላክ እንደ ሆንህ፥ ልባ​ቸ​ው​ንም ደግሞ እንደ መለ​ስህ፤ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ ስማኝ፤ አቤቱ፥ ስማኝ” አለ። እሳ​ትም ከሰ​ማይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወረ​ደች፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ እን​ጨ​ቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በላች፤ በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ያለ​ውን ውኃ፥ አፈ​ሩ​ንም ላሰች። ሕዝ​ቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት እርሱ አም​ላክ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ ነው” አሉ።