እኔ ነጻ አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያየሁ አይደለሁምን? እናንተስ በጌታችን ሥራዬ አይደላችሁምን? ለሌሎች ሐዋርያቸው ባልሆንም ለእናንተስ ሐዋርያችሁ እኔ ነኝ፤ በጌታችን የሐዋርያነቴ ማኅተም እናንተ ናችሁና። ለሚከራከሩኝ መልሴ እንዲህ ነው። በውኑ ልንበላና ልንጠጣ አይገባንምን? እንደ ሌሎች ሐዋርያት ሁሉና፥ እንደ ጌታችን ወንድሞች እንደ ኬፋም ከሴቶች እኅታችንን ይዘን ልንዞር አይገባንምን? ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን? የሚያገለግልም ምግቡን ያገኝ ዘንድ ነው፤ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? መንጋውንስ ጠብቆ ወተቱን የማይጠጣ ማን ነው? በውኑ ለሰው ይምሰል እናገራለሁን? የሙሴ መጽሐፍ ኦሪትስ እንዲህ ብሎ የለምን፦ “እህልህን በምታበራይበት ጊዜ የበሬውን አፉን አትሰረው።” እንግዲህ ይህን የጻፈ ለእግዚአብሔር በሬ አሳዝኖት ነውን? ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ፥ የሚያበራይም እንዲካፈል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው በእውነት ስለ እኛ ተጽፎአል። እኛ መንፈሳዊውን ነገር ከዘራንላችሁ ሥጋዊውን ነገር ብናጭድ ታላቅ ነገር ነውን? በእኛ ሹመት ሌላ የሚቀድመን ከሆነ የሚሻላችሁን እናንተ ታውቃላችሁ፤ እኔ ይህን አልፈለግሁትም፤ ነገር ግን የክርስቶስን ትምህርት እንዳላሰናክል በሁሉ እታገሣለሁ።
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 9 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 9
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 9:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች