ያገቡትንም በእግዚአብሔር ትእዛዝ አዝዛቸዋለሁ፤ በራሴ ትእዛዝም አይደለም፤ ሚስትም ከባልዋ አትፋታ። ከተፋታችም ብቻዋን ትኑር፤ ያለዚያ ከባልዋ ጋር ትታረቅ፤ ባልም ሚስቱን አይፍታ። ሌላውን ግን ከራሴ እናገራለሁ፤ ከጌታችንም አይደለም፤ ከወንድሞቻችን መካከል የማታምን፥ ባልዋንም የምታፈቅር ከእርሱም ጋር ለመኖር የምትወድ ሚስት ያለችው ሰው ቢኖር ሚስቱን አይፍታ። ሴቲቱም የማያምንና ሚስቱንም የሚያፈቅር ከእርስዋም ጋር ሊኖር የሚወድ ባል ቢኖራት ባልዋን አትፍታ። የማያምን ባል በሚስቱ ይቀደሳልና፤ የማታምን ሚስትም በባልዋ ትቀደሳለችና፤ ያለዚያማ ልጆቻቸው ርኩሳን ይሆናሉ፤ አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው። የማያምን ግን ቢፈታ ይፍታ፤ ወንድምና እኅት እግዚአብሔር ለሰላም ስለ ጠራቸው እንደዚህ ላለ ግብር አይገዙምና። ሚስትም ባልዋን ታድነው እንደ ሆነ አታውቅምና፤ ባልም ሚስቱን ያድናት እንደ ሆነ አያውቅምና።
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 7 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 7
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 7:10-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች