ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 6:15-18

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 6:15-18 አማ2000

ሥጋ​ችሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን አካል ወስ​ዳ​ችሁ የአ​መ​ን​ዝራ አካል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ች​ሁን? አይ​ገ​ባም። ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር የተ​ገ​ናኘ ከእ​ር​ስዋ ጋር አንድ አካል እን​ዲ​ሆን አታ​ው​ቁ​ምን? መጽ​ሐፍ፥ “ሁለቱ አንድ አካል ይሆ​ናሉ” ብሎ​አ​ልና። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የተ​ዋ​ሐደ ግን ከእ​ርሱ ጋር አንድ መን​ፈስ ይሆ​ናል። ከዝ​ሙት ራቁ፤ ኀጢ​አት የሚ​ሠራ ሰው ሁሉ ከሥ​ጋው ውጭ ይሠ​ራ​ልና፤ ዝሙ​ትን የሚ​ሠራ ግን ራሱ በሥ​ጋው ላይ ኀጢ​አ​ትን ይሠ​ራል።