የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:15-18

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:15-18 አማ05

ሰውነታችሁ የክርስቶስ አካል ክፍል መሆኑን ታውቁ የለምን? ታዲያ፥ የክርስቶስን አካል ክፍል ወስጄ የአመንዝራ ሴት አካል ክፍል እንዲሆን ላደርገው ይገባልን? ከቶ አይገባም! ከአመንዝራ ሴት ጋር የሚገናኝ ሰው ከእርስዋ ጋር አንድ አካል መሆኑን ታውቁ የለምን? “ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ” ተብሎ ተጽፎአልና። ከጌታ ኢየሱስ ጋር የሚተባበር ሰው ግን ከእርሱ ጋር በመንፈስ አንድ ይሆናል። ስለዚህ ከዝሙት ራቁ፤ ሰው የሚያደርገው ሌላው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጪ የሚደረግ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ሰው ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአት ይሠራል፤