የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 2:6-15

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 2:6-15 አማ2000

ለዐ​ዋ​ቆች ጥበ​ብን እን​ነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለን፤ ነገር ግን የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላ​ቸ​ውን የዚ​ህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይ​ደ​ለም። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ከዘ​መ​ናት በፊት ለክ​ብ​ራ​ችን የወ​ሰ​ነ​ውን ተሰ​ው​ሮም የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በም​ሥ​ጢር እን​ና​ገ​ራ​ለን። የዚህ ዓለም ሹሞ​ችም አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ይህ​ንስ ቢያ​ውቁ ኑሮ የክ​ብር ባለ​ቤ​ትን ባል​ሰ​ቀ​ሉ​ትም ነበር። ነገር ግን መጽ​ሐፍ፥ “ዐይን ያላ​የው፥ ጆሮም ያል​ሰ​ማው፥ በሰ​ውም ልቡና ያል​ታ​ሰበ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ወ​ዱት ያዘ​ጋ​ጀው ነው።” ብሎ የለ​ምን? ለእ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ፈሱ ገለ​ጠ​ልን፤ መን​ፈስ ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጥልቅ ምሥ​ጢ​ሩን ያው​ቃ​ልና። በሰው ልቡና ያለ​ውን የሚ​ያ​ውቅ ሰው ማን ነው? በእ​ርሱ ያለ​ችው ነፍሱ ናት እንጂ፤ እን​ዲ​ሁም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በቀር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳብ የሚ​ያ​ውቅ የለም። እኛ የዚ​ህን ዓለም መን​ፈስ የተ​ቀ​በ​ልን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ንን ጸጋ እና​ውቅ ዘንድ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሆ​ነ​ውን መን​ፈስ ተቀ​በ​ልን። ይህም ትም​ህ​ር​ታ​ችን ከሰው የተ​ገኘ ትም​ህ​ርት አይ​ደ​ለም፤ የአ​ነ​ጋ​ገር ጥበ​ብም አይ​ደ​ለም፤ መን​ፈስ ቅዱስ የገ​ለ​ጸው ትም​ህ​ርት ነው እንጂ፤ መን​ፈ​ሳዊ ጥበ​ብም ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ የሚ​ሆ​ነ​ውን መር​ም​ረው ለሚ​ያ​ውቁ ለመ​ን​ፈ​ሳ​ው​ያን ነው። ለሥ​ጋዊ ሰው ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነገር ሞኝ​ነት ይመ​ስ​ለ​ዋ​ልና፥ አይ​ቀ​በ​ለ​ውም፤ በመ​ን​ፈ​ስም የሚ​መ​ረ​መር ስለ​ሆነ ሊያ​ውቅ አይ​ች​ልም። መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በት ሰው ግን ሁሉን ይመ​ረ​ም​ራል፤ እር​ሱን ግን የሚ​መ​ረ​ም​ረው የለም።