ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 11:27-32

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 11:27-32 አማ2000

አሁ​ንም ሳይ​ገ​ባው ይህን ኅብ​ስት የበላ፥ ይህ​ንም ጽዋ የጠጣ የጌ​ታ​ችን ሥጋ​ውና ደሙ ስለ​ሆነ ዕዳ አለ​በት። አሁ​ንም ሰው ራሱን መር​ም​ሮና አን​ጽቶ ከዚህ ኅብ​ስት ይብላ፤ ከዚ​ህም ጽዋ ይጠጣ። ሳይ​ገ​ባው፥ የጌ​ታ​ችን ሥጋም እንደ ሆነ ሳያ​ውቅ፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም ሳያ​ነጻ፥ የሚ​በ​ላና የሚ​ጠጣ ለራሱ ፍር​ዱ​ንና መቅ​ሠ​ፍ​ቱን ይበ​ላል፤ ይጠ​ጣ​ልም። ስለ​ዚህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የደ​ከ​ሙና የታ​መሙ ብዙ​ዎች ናቸው፤ ብዙ​ዎ​ችም በድ​ን​ገት አን​ቀ​ላ​ፍ​ተ​ዋል። እኛ በራ​ሳ​ችን ብን​ፈ​ርድ ኖሮ ባል​ተ​ፈ​ረ​ደ​ብ​ንም ነበር። ነገር ግን በተ​ፈ​ረ​ደ​ብን ጊዜ ከዓ​ለም ጋር እን​ዳ​ን​ኰ​ነን በጌታ እን​ገ​ሠ​ጻ​ለን።