ወንድሞች! አሁንም ጣዖት ከማምለክ ሽሹ። ለዐዋቂዎች እንደሚነገር እነግራችኋለሁ፤ ትክክለኛውንም እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ። ይህ የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር አንድ አይደለምን? የምንፈትተው ይህስ ኅብስት ከክርስቶስ ሥጋ ጋር አንድ አይደለምን? ኅብስቱ አንድ እንደ ሆነ እንዲሁ እኛም ብዙዎች ስንሆን አንድ አካል ነን፤ ሁላችን ከአንድ ኅብስት እንቀበላለንና። እስራኤል ዘሥጋን ተመልከቱ፤ መሥዋዕቱን ይበላሉ፤ ከመሠዊያውም ጋር አንድ ይሆኑ አልነበረምን? እንግዲህ ምን እንላለን? ለጣዖታት የሚሠዋ መሥዋዕት ከንቱ ነው፤ ጣዖቶቻቸውም ከንቱ ናቸው። አሕዛብም የሚሠዉ ለአጋንንት ነው እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም፤ ነገር ግን የአጋንንት ተባባሪዎች እንድትሆኑ አልፈቅድላችሁም። የእግዚአብሔርን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ አንድ አድርጋችሁ መጠጣት አትችሉም፤ የእግዚአብሔርን ማዕድና የአጋንንትንም ማዕድ በአንድነት ልትበሉ አትችሉም። እንግዲህ እግዚአብሔርን እናስቀናውን? በውኑ እኛ ከእርሱ እንበረታለን?
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 10 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 10
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 10:14-22
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos