ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 1
1
1በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊሆን ከተጠራ ከጳውሎስና ከወንድማችን ከሶስቴንስ፥ 2በቆሮንቶስ ሀገር ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለከበሩና ቅዱሳን ለተባሉ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ለሚጠሩ ሁሉ፥ 3ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
4ስለ እናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ ስለተሰጣችሁ ጸጋ ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። 5በአነጋገር ሁሉ፥ በዕውቀትም ሁሉ ከብራችሁበታልና። 6ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ እንደ ጸና መጠን። 7ፍጹማንም እንድትሆኑ#“ፍጹማንም እንድትሆኑ” የሚለው በግሪኩ የለም። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስንም መምጣት ተስፋ አድርጋችሁ ፍጹም ጸጋን እንዳታጡ፥ 8እርሱም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነውር ትገኙ ዘንድ እስከ ፍጻሜ ያጸናችኋል። 9ከልጁ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።
መለያየት እንደማይገባ
10ወንድሞቻችን! አንድ ቃል እንድትናገሩ፥ እንዳታዝኑ፥ ፍጹማንም እንድትሆኑ፥ ሁላችሁንም፦ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፤ እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆናችሁ ኑሩ። 11ወንድሞቻችን ሆይ! እንደምትጣሉና እንደምትከራከሩ ከቀሎኤስ ወገኖች ስለ እናንተ ነገሩኝ። 12#የሐዋ. 18፥24። እነሆ፥ እርስ በርሳችሁ፥ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤ እኔ የአጵሎስ ነኝ፤ እኔ የኬፋ ነኝ፤ እኔ የክርስቶስ ነኝ” የምትሉትን እነግራችኋለሁ። 13ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ወይስ በውኑ ጳውሎስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠምቃችኋልን? 14#የሐዋ. 18፥8፤ 19፥29፤ ሮሜ 16፥23። ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ከእናንተ ወገን ሌላ ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። 15በእርሱ ስም ተጠመቅን የሚል እንዳይኖር። 16#1ቆሮ. 16፥15። ነገር ግን የእስጢፋኖስን ቤተ ሰብእ አጥምቄአለሁ፤ እንግዲህ ሌላም ያጠመቅሁት እንዳለ አላውቅም።
ስለ መስቀል
17ክርስቶስ ወንጌልን ለመስበክ እንጂ ለማጥመቅ አልላከኝምና፥ የክርስቶስን መስቀሉን ከንቱ እንዳናደርግ ነገርን በማራቀቅ አይደለም። 18የመስቀሉ ነገር በሚጠፉ ሰዎች ዘንድ ስንፍና ነውና፥ ለምንድነው ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው። 19#ኢሳ. 29፥14። መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “እኔ የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የመካሪዎችንም ምክር እንቃለሁ።” 20#ኢዮብ 12፥17፤ ኢሳ. 19፥12፤ 33፥18፤ 44፥25። እንግዲህ ጥበበኛ ማን ነው? ጸሓፊስ ማን ነው? ይህን ዓለምስ የሚመረምረው ማን ነው? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ስንፍና አላደረገውምን? 21ሰዎች በጥበባቸው በማያውቁት በእግዚአብሔር ጥበብ ስንፍና በሚመስላቸው ትምህርት ያመኑትን ሊያድናቸው እግዚአብሔር ወድዶአልና። 22አይሁድ ምልክትን ይጠይቃሉ፤ የጽርዕ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ። 23እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ስንፍና ነው። 24ለእኛ ለዳንነው#ግሪኩ “ለተጠሩት ግን ...” ይላል። ግን ከአይሁድ፥ ከአረሚም ብንሆን ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ የእግዚአብሔርም ጥበብ ነው። 25የእግዚአብሔር ስንፍና ከሰው ይልቅ ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።
26ወንድሞቻችን! እንግዲህ እንዴት እንደ ተጠራችሁ እዩ፤ በሥጋ እጅግ ብዙዎች ዐዋቂዎች አይደላችሁምና፥ ብዙዎች ኀያላንም አይደላችሁምና፥ በዘመድም ብዙዎች ደጋጎች አይደላችሁምና። 27ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ሊያሳፍር የዚህን ዓለም ሰነፎች መረጠ፤ ኀይለኞችንም ያሳፍር ዘንድ እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ደካሞች መረጠ። 28አለን የሚሉትንም ያሳፍር ዘንድ ዘመድ የሌላቸውንና የተናቁትን፥ ከቍጥርም ያልገቡትን እግዚአብሔር መረጠ። 29ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ። 30እናንተም በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ናችሁ፤ በእርሱም ከእግዚአብሔር ጥበብንና ጽድቅን፥ ቅድስናንና ቤዛነትን አገኘን። 31#ኤር. 9፥24። መጽሐፍ እንደ አለው ይሆን ዘንድ “የሚመካስ በእግዚአብሔር ይመካ።”
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 1: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ