መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 3
3
1በኬብሮን ለዳዊት የተወለዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኵሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዶለህያ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዳንኤል” ይላል። ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፥ 2ሦስተኛው አቤሴሎም ከጌድሶር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ፥ አራተኛው አዶንያስ ከአጊት፥ 3አምስተኛው ሰፋጥያስ ከአቢጣል፥ ስድስተኛው ይትርኃም ከሚስቱ ከዔግላ። 4እነዚህ ስድስቱ በኬብሮን ተወለዱለት፤ በዚያም ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ። 5እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚል ልጅ ከቤርሳቤህ ስማዕ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፥ አራት፤ 6ኢያቤሔር፥ ኤልሳማ፥ ኤሊፋላት፥ 7ናጌል፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥ 8ኤልሳማ፥ ኤሊዳ፥ ኤልፋሌጥ፥ ዘጠኝ። 9እነዚህ ሁሉ ከቁባቶቹ ልጆች በቀር የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕማርም እኅታቸው ነበረች።
10የሰሎሞንም ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥ ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮሣፍጥ፥ 11ልጁ ኢዮራም፥ ልጁ አካዝያስ፥ ልጁ ኢዮአስ፥ 12ልጁ አሜስያስ፥ ልጁ ዓዛርያስ፥ ልጁ ኢዮአታም፥ 13ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝቅያስ፥ ልጁ ምናሴ፥ 14ልጁ አሞጽ፥ ልጁ ኢዮስያስ። 15የኢዮስያስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛውም ኢዮአቄም፥ ሦስተኛውም ሴዴቅያስ፥ አራተኛውም ሰሎም። 16የኢዮአቄምም ልጆች፤ ልጁ ኢኮንያን፥ ልጁ ሴዴቅያስ። 17የኢኮንያንም ልጆች አሤር፥ ሰላትያል፥ 18መልኪራም፥ ፈዳያ፥ ሳንሳሮ፥ ይቃምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ። 19የፈዳያም ልጆች ዘሩባቤልና ሰሜኤ ነበሩ፤ የዘሩባቤልም ልጆች፤ ሜሱላም፥ ሐናንያ፥ እኅታቸውም ሰሎሚት። 20አሱባ፥ አሄል፥ በራክያ፥ ሐሳድያ፥ አስቦሴድ አምስት#በምዕ. 3 ቍ. 19 ያሉትን ደምሮ ስምንት የሚል ዘርዕ አለ። ናቸው። 21የሐናንያም ልጆች ፈላጥያና ልጁ ኢያሴያ ነበሩ። ረፋያ ልጁ፥ አርና ልጁ፥ አብድዩ ልጁ፥ ሴኬንያ ልጁ። 22የሴኬንያም ልጅ ሰማዕያ ነበረ። የሰማዕያም ልጆች ሐጡስ፥ ኢዮሔል፥ ቤርያሕ፥ ነዋድያ፥ ሳፌጥ ስድስት ነበሩ። 23የነዋድያ ልጆች ኤልዮዔንኢ፥ ሕዝቅያስ፥ ዓዝሪቃም ሦስት ነበሩ። 24የኤልዮዔናኢም ልጆች አዳይያ፥ ኤልያሴብ፥ ፈላያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐናን፥ ዶላያ፥ ዓናኒ ሰባት ነበሩ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 3: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ