የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 3

3
1በኬ​ብ​ሮን ለዳ​ዊት የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። በኵሩ አም​ኖን ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዶለ​ህያ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዳን​ኤል” ይላል። ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቢ​ግያ፥ 2ሦስ​ተ​ኛው አቤ​ሴ​ሎም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከተ​ል​ማይ ልጅ ከመ​ዓካ፥ አራ​ተ​ኛው አዶ​ን​ያስ ከአ​ጊት፥ 3አም​ስ​ተ​ኛው ሰፋ​ጥ​ያስ ከአ​ቢ​ጣል፥ ስድ​ስ​ተ​ኛው ይት​ር​ኃም ከሚ​ስቱ ከዔ​ግላ። 4እነ​ዚህ ስድ​ስቱ በኬ​ብ​ሮን ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በዚ​ያም ሰባት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ። 5እነ​ዚህ ደግሞ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ ከዓ​ሚል ልጅ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ስማዕ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፥ አራት፤ 6ኢያ​ቤ​ሔር፥ ኤል​ሳማ፥ ኤሊ​ፋ​ላት፥ 7ናጌል፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥ 8ኤል​ሳማ፥ ኤሊዳ፥ ኤል​ፋ​ሌጥ፥ ዘጠኝ። 9እነ​ዚህ ሁሉ ከቁ​ባ​ቶቹ ልጆች በቀር የዳ​ዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕ​ማ​ርም እኅ​ታ​ቸው ነበ​ረች።
10የሰ​ሎ​ሞ​ንም ልጅ ሮብ​ዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥ ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ 11ልጁ ኢዮ​ራም፥ ልጁ አካ​ዝ​ያስ፥ ልጁ ኢዮ​አስ፥ 12ልጁ አሜ​ስ​ያስ፥ ልጁ ዓዛ​ር​ያስ፥ ልጁ ኢዮ​አ​ታም፥ 13ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ ልጁ ምናሴ፥ 14ልጁ አሞጽ፥ ልጁ ኢዮ​ስ​ያስ። 15የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐ​ናን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ኢዮ​አ​ቄም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አራ​ተ​ኛ​ውም ሰሎም። 16የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምም ልጆች፤ ልጁ ኢኮ​ን​ያን፥ ልጁ ሴዴ​ቅ​ያስ። 17የኢ​ኮ​ን​ያ​ንም ልጆች አሤር፥ ሰላ​ት​ያል፥ 18መል​ኪ​ራም፥ ፈዳያ፥ ሳን​ሳሮ፥ ይቃ​ምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳ​ብያ ነበሩ። 19የፈ​ዳ​ያም ልጆች ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ሰሜኤ ነበሩ፤ የዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልም ልጆች፤ ሜሱ​ላም፥ ሐና​ንያ፥ እኅ​ታ​ቸ​ውም ሰሎ​ሚት። 20አሱባ፥ አሄል፥ በራ​ክያ፥ ሐሳ​ድያ፥ አስ​ቦ​ሴድ አም​ስት#በምዕ. 3 ቍ. 19 ያሉ​ትን ደምሮ ስም​ንት የሚል ዘርዕ አለ። ናቸው። 21የሐ​ና​ን​ያም ልጆች ፈላ​ጥ​ያና ልጁ ኢያ​ሴያ ነበሩ። ረፋያ ልጁ፥ አርና ልጁ፥ አብ​ድዩ ልጁ፥ ሴኬ​ንያ ልጁ። 22የሴ​ኬ​ን​ያም ልጅ ሰማ​ዕያ ነበረ። የሰ​ማ​ዕ​ያም ልጆች ሐጡስ፥ ኢዮ​ሔል፥ ቤር​ያሕ፥ ነዋ​ድያ፥ ሳፌጥ ስድ​ስት ነበሩ። 23የነ​ዋ​ድያ ልጆች ኤል​ዮ​ዔ​ንኢ፥ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ ዓዝ​ሪ​ቃም ሦስት ነበሩ። 24የኤ​ል​ዮ​ዔ​ና​ኢም ልጆች አዳ​ይያ፥ ኤል​ያ​ሴብ፥ ፈላያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐ​ናን፥ ዶላያ፥ ዓናኒ ሰባት ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ