መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 22:11-13

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 22:11-13 አማ2000

አሁ​ንም ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አን​ተም እንደ ተና​ገ​ረው ያከ​ና​ው​ን​ልህ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ። ብቻ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ይስ​ጥህ፤ መን​ግ​ሥ​ት​ህ​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ያጽና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እስ​ራ​ኤል ሙሴን ያዘ​ዘ​ውን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ ብት​ጠ​ነ​ቀቅ በዚ​ያን ጊዜ ይከ​ና​ወ​ን​ል​ሃል፤ አይ​ዞህ፥ በርታ፤ አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።